Logo
FastMereja
የአሜሪካ መንግስት በህወሓት አመራሮች ላይ የቪዛ ማዕቀብ ጣለ
#fastmereja I የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰሜን ኢትዮጵያ የሰላም ሂደትን እያደናቀፉ ነው ባላቸው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ ያነጣጠረ የቪዛ ገደብ ማዕቀብ መጣሉን ዛሬ ሐሙስ አስታውቋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፥ በህወሓት እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል እየተፈጠረ ያለው ከፍተኛ ውጥረት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ሊቀሰቅስና የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ገልጿል። ይሄው የቪዛ ማዕቀብ ፖሊሲ በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በሚያደናቅፉ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጃቸው ባለበት ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ተነግሯል።

ባለፈው ወር ህወሓት፣ የፌደራል መንግስቱን የሰላም ስምምነት ድንጋጌ የሚጥስ እርምጃ በመውሰድ የክልሉን የፖለቲካ አስተዳደር በበላይነት መቆጣጠሩ ይታወሳል። ፓርቲው ከ2013-2015 ዓ.ም የነበረውን የጦርነት ወቅት ቀድሞ የነበረውን የምክር ቤት መዋቅር በድጋሚ ማቋቋሙንና የምክር ቤቱም የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑትን ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡን አስታውቆ ነበር።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.