Logo
SeledaPost
ሰበር መረጃ‼️አሜሪካ በህወሓት ላይ እገዳ‼️

አሜሪካ በህወሓት (TPLF) አባላት እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ እገዳ ጣለች።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ እንዲሁም በመላ ቀጠና ያለውን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥለዋል ባሏቸው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላት እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ገደብ መጣሉን አስታውቀዋል።

ውሳኔው የተላለፈው በስደተኞችና ዜግነት አዋጅ አንቀጽ 212(a)(3)(C) በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ እገዳው በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በሚያስተጓጉሉ " አክራሪ አቋም " ባላቸው አባላትና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ በህወሓት አመራሮችና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የሰሜን ኢትዮጵያን ሰላም ዳግም ስጋት ላይ መጣሉን ጠቅሷል።

በተለይም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በትግራይ የፀጥታ ኃይሎች (TSF) እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) መካከል የተከሰተው ቀጥተኛ ግጭት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የተገኘውን አንጻራዊ መረጋጋት የሚፈታተን መሆኑ አመልክቷል።

አሜሪካ በሰላምና በክብር መኖር የሚፈልገውን የትግራይን ጨምሮ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መደገፏን እንደምትቀጥል የገለጸው መግለጫው፤ በክልሉ ሰላምና መረጋጋትን በሚያናጉ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን ያሉትን አማራጮች ሁሉ ጥቅም ላይ እንደምታውል አስታውቃለች።

የቪዛ ማዕቀብ የተጣለባቸው የህወሓት (TPLF) አመራሮች እና ቤተሰቦቻቸው ስም በይፋ አልተገለጸም።

Seledadotio
Seledadotio
21 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.