Logo
Getu Temesgen
“በክርስቲያኖ ሮናልዶ የቡድኑን ፍላጎት ወደ ጎን በመተው የግል ስኬቱን ብቻ ያስቀድማል” - ቲዬሪ ኦንሪ
#ethiopia | የፈረንሳይ እና የአርሰናል እግር ኳስ የምንግዜውም ምርጥ አጥቂ ቲዬሪ ኦንሪ ፣ ፖርቱጋል ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር 1 ለ 1 ከተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በኋላ በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ከባድ ትችት ሰንዝሯል።

ኦንሪ የፖርቱጋሉን አጥቂ እና አምበል “የቡድኑን ፍላጎት ወደ ጎን በመተው የግል ስኬቱን ብቻ ያስቀድማል” ሲል ከሷል።

​በሂውስተን በተደረገው በዚህ ጨዋታ ፖርቱጋል ነጥብ መጣሏ በምድብ ‘ኬ’ ውስጥ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለማለፍ የምታደርገውን ጉዞ አስቸጋሪ አድርጎባታል።

ከጨዋታው በኋላ በፎክስ ስፖርት የየዕለቱ ትንተና ላይ የቀረበው ቲዬሪ ኦንሪ፣ በጨዋታው ላይ የታየን አንድ የተወሰነ አጋጣሚ በማንሳት የሮናልዶ ግለኝነት ለፖርቱጋል የማጥቃት መስመር መበላሸት ዋናው ምክንያት መሆኑን በምሳሌነት አስረድቷል።

​ይህ የኦንሪ አስተያየት፣ በክርስቲያኖ ሮናልዶ የግል ክብረ ወሰኖችን የማሳደድ ጉጉት እና በፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ስኬት ዙሪያ ሲደረግ የነበረውን ክርክር ይበልጥ እንዲጋጋል አድርጎታል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.