የአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት የነዳጅ ዋጋን ቀነሰ
አሜሪካ እና ኢራን የሆርሙዝ የባህር መስመርን ለመክፈትና ጦርነቱን ለማቆም የስምምነት ማዕቀፍ ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል።
ስምምነቱን ተከትሎ የጃፓንና የደቡብ ኮሪያ አክሲዮን ገበያዎች እስከ 5.7 በመቶ የደረሰ ታሪካዊ ጭማሪ አሳይተዋል።
በአንጻሩ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ4.5 በመቶ በመቀነስ በአንድ በርሜል ከ83.40 ዶላር በታች ወርዷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ የተጣለው የባህር ኃይል እገዳ እንዲነሳ ማዘዛቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ ይፋዊው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አርብ ዕለት በስዊዘርላንድ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ስምምነቱ ሊባኖስን ጨምሮ የተኩስ አቁም ማድረግን፣ የማዕቀብ መነሳትን እና የ24 ቢሊየን ዶላር የኢራን ሀብት መልቀቅን ያጠቃልላል ተብሏል።
የባህር መስመሩ መከፈቱ የዓለምን የነዳጅ እጥረት የሚያቃልል ቢሆንም፤ የተከማቹ መርከቦችን ለማፅዳትና የባህር ውስጥ ፈንጂዎችን ስጋት ለመቅረፍ ግን ወራትን ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎች አስታውቀዋል።
ሳራ ዮሐንስ
Seledadotio

4 days ago