(ዘ-ሐበሻ ዜና) የክሊቭላንድ ካቫሊየርስ ኮከብ ተጫዋች የሆነው ጀምስ ሀርደን፣ በህገ-ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ በተሽከርካሪ ውስጥ ይዞ በመገኘቱ ቅዳሜ ዕለት በሂዩስተን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የ36 ዓመቱ ሀርደን ከሌሊቱ 9፡41 ላይ የተያዘ ሲሆን፣ ከሽጉጥ መያዣው (holster) ውጭ በግልጽ በሚታይ ሁኔታ ሽጉጥ አስቀምጦ በመገኘቱ ክስ ቀርቦበታል። ሆኖም 100 ዶላር ዋስ በማስያዝ ከእስር መለቀቁን የሃሪስ ካውንቲ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሰነዶች ያሳያሉ።
ተጫዋቹ በቀጣዩ ሰኔ 15 ፍርድ ቤት የሚቀርብ ይሆናል። ክሊቭላንድ ካቫሊየርስ ባወጣው መግለጫ ስለእስሩ መስማቱን እና ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር ግንኙነት መፍጠሩን ጠቅሶ፣ ተጨማሪ መረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን አስታውቋል።
17ኛውን የኤንቢኤ የውድድር ዘመኑን በቅርቡ ያጠናቀቀው ሀርደን፣ በቀጣዩ ዓመት በ42.3 ሚሊዮን ዶላር በክሊቭላንድ ለመቀጠል የሚያስችለውን የውል ማራዘሚያ አማራጭ የመጠቀም መብት አለው። የ2017-18 የውድድር ዘመን ኮከብ የነበረው እና 11 ጊዜ በኦል-ስታር (All-Star) የተመረጠው ሀርደን፣ ክሊቭላንድ በኒውዮርክ ኒክስ ተሸንፎ ከምስራቅ ኮንፈረንስ ፍጻሜ ከተሰናበተ በኋላ በክለቡ ረዘም ላለ ጊዜ ለመቆየት ፍላጎት እንዳለው ማሳወቁ ይታወሳል።

5 days ago