ከብረት የጠጠረ፤ በፈተና ነጥሮ የወጣ፤ የማይበገረው ሠራዊታችን
******************
ኢትዮጵያ በጽኑ መሠረት ላይ የምትቆመው እና ሉዓላዊነቷ ተከብሮ የምትኖረው፣ የሕይወት መሥዋዕትነትን በቆራጥነት በሚቀበሉ፣ ከብረት የጠነከረ ዲሲፕሊን ባላቸው እና ሀገርን ከምንም በላይ በሚያስቀድሙ የቁርጥ ቀን ልጆቿ ትከሻ ላይ ነው።
ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በቀጣናው የኃይል ሚዛን ውስጥ ማንም በድፍረት የማይገዳደረው፣ ሞገሳም እና ሁለንተናዊ ብቃት የተላበሰ ታላቅ ኃይል ነው።
ይህ የማይበገር ጋሻችን፣ የውኃውን ሙላት፣ የየብስን ስፋት እና የአየሩን ከፍታ በሚመጥን ቁመና፣ ኢትዮጵያን አስከብሮ ለማቆየት የሚያስችል አስተማማኝ አቅም ገንብቷል።
የዚህ ታላቅ ሠራዊት እውነተኛ የብቃት ምንጭ የመነጨው ሀገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ ከተወሰደው ጥልቅ ተቋማዊ ተሃድሶ ነው።
ለዘመናት የፖለቲካ ሥርዓት ጠባቂ እና የፓርቲ ርዕዮተ ዓለም አገልጋይ ሆኖ የቆየው የፀጥታ እና መከላከያ ተቋማችን፣ በለውጡ ውስጥ አልፎ ተልዕኮውን በሚገባ አጥርቷል።
ዛሬ ላይ ሠራዊታችን መሣሪያውን የሚያነሣው ሕገ-መንግሥቱን፣ የሀገርን ሉዓላዊነት እና የዜጎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ብቻ ነው። ይህ መሠረታዊ የዕይታ ሽግግር፣ ሠራዊቱን "ራስ አስቀጥል እና ሀገር አስቀጣይ" ወደሆነ ተቋማዊ ልዕልና አሸጋግሮታል። ወታደሩ የሀገርን እና የትውልድን አደራ በልቡ ሰሌዳ ላይ ጽፎ፣ ትልቅ ብሔራዊ ኃላፊነት ለመሸከም ተሰልፏል።
ከተልዕኮ ጥራቱ ባሻገር፣ በመዋቅራዊ እና ቴክኖሎጂያዊ አቅም ግንባታው ያሳየው እመርታ አስደናቂ ነው።
የፀጥታ እና ደኅንነት ተቋማትን ለማዘመን በተሠራው ሰፊ ሥራ፣ ሠራዊታችን የዘመኑን ቴክኖሎጂ በማላመድ እና አዳዲስ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር የሀገርን አቅም በከፍተኛ ደረጃ አግዝፏል።
ለሠራዊቱ የሚያስፈልጉ ትጥቆችን እና ስንቆችን በራስ አቅም ለማሟላት በተደረገው ርብርብ፣ ዘመናዊ ትጥቅን ከብረት የጠነከረ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ጋር አስተባብሮ የያዘ ኃይል መፍጠር ተችሏል።
ይህ ሥነ-ምግባር እና ቴክኖሎጂያዊ ብቃት፣ ኢትዮጵያን ከየትኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመከላከል የሚያስችል አቅም ፈጥሯል።
በአጠቃላይ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የትናንቱን የፓርቲ አገልጋይነት ካባ አውልቆ፣ "ሀገርን ማስቀደም" በሚል ጥልቅ መንፈስ የታነፀ የዘመናችን ዐርበኛ ሆኗል።
በቀጣናው የኃይል ሚዛን ላይ ትልቅ ስፍራ ይዞ፣ ማንም የማይደፍረው እና በጠላቶቹ ዘንድ አስፈሪ የሆነው ይህ ሠራዊት፣ የኢትዮጵያ ሕልውና የማይናወጥበት ጽኑ ዓምድ ነው።
የኢትዮጵያውያን ደኅንነት፣ ክብር እና ሉዓላዊነት፣ ከፖለቲካ ጫና በፀዳ፣ ተልዕኮውን ጠንቅቆ ባወቀ፣ በጠንካራ ዲሲፕሊን ታንጾ ሀገርን እና ትውልድን ለማገልገል ቆርጦ በተነሣው ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን እጅ አስተማማኝ ከለላ አግኝቷል።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #defense #endf

3 hours ago