የብሔራዊ አልኮል ቡድን የሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግን በበላይነት አጠናቀቀ
#ethiopia | የ2018 ዓ.ም የደራባ ሚድሮክ ሲሚንቶ የሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል።
በfinal ጨዋታው ብሔራዊ አልኮል የፌዴራል ማረሚያ ቤትን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት የዘንድሮው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን መሆን ችሏል።
በሁለት ዙሮች ተከፍሎ የተከናወነው የዘንድሮው የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻው ዙር ውድድር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተስተናገደ ሲሆን፣ ሁለተኛውና የማጠቃለያው ምዕራፍ ደግሞ በአዲስ አበባ ትንሻ ስታዲየም ፍጻሜውን አግኝቷል።
በዕለቱ በተከናወነው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ በወጣት ስፖርተኞች ምልመላና በታዳጊዎች ዘርፍ ላሳየው ከፍተኛ ተሳትፎ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
በሌላ በኩል የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ክለብ ላለፉት 40 ዓመታት በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ በተለይም ለቮሊቦል ስፖርት ዕድገትና መኖር ላበረከተው ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽኦ እንዲሁም ለ40ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉ መታሰቢያ የሚሆን ልዩ የክብር ዋንጫ ተበርክቶለታል።
የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሉ ሸዋዬ እንደገለጹት፣ ዘንድሮ ውድድሩ በበጀት እጥረት ምክንያት በአራት ክለቦች ብቻ የተገደበ ቢሆንም በታዩት ድንቅ ወጣት ተጫዋቾችና በነበረው ጠንካራ ፉክክር በጥሩ ጎኑ የሚገመገም ነው።
ኃላፊው አክለውም በቀጣይ ዓመት የወንዶችንና የሴቶችን ውድድር በአንድ ላይ በማቀናጀት ስፖርቱ የሚገባውን የመንግሥትና የባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲያገኝ ሰፊ የዝግጅት ሥራዎች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።
#volleyball #sport #ethiopiansport #champions #womensvolleyball #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

16 hours ago