በነዳጅ ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በነበሩ አምስት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ እንዲቋረጥ ተወሰነ
#ethiopia | በነዳጅ እጥረት መከሰት እና በከባድ የሙስና ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው በነበሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ነጋዴዎች ላይ የቀረበው ሦስተኛው የክስ መዝገብ እንዲቋረጥ የፍትሕ ሚኒስቴር ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ይህ የክስ መቋረጥ ውሳኔ የተላለፈው የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ዲባራ ፉፋን እና በፌደራል ፖሊስ አማካኝነት የይፈለጋሉ ማስታወቂያ የወጣባቸውን ሁለት ተከሳሾችን ጨምሮ በአጠቃላይ በአምስት ተከሳሾች ላይ ነው።
የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በጻፈው ይፋዊ ደብዳቤ እንዳስታወቀው፣ ውሳኔው የተላለፈው ከ9ኛ እና ከ10ኛ ተከሳሾች የቀረበን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ነው።
የቀረበው አቤቱታ ከተመረመረ በኋላ ምክንያቱ አሳማኝ ሆኖ በመገኘቱ እና በተከሳሾቹ ላይ የተሰነዘረውን የጥፋተኝነት ክስ ለማስረዳት የሚያስችል በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ ክሱ እንዲቋረጥ ተወስኗል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 3(ሀ) እና በፍትሕ ሚኒስቴር የወንጀል መዝገቦች ውሳኔ አሰጣጥ መመሪያ መሠረት ነው።
በዚህም መሠረት ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረገላቸው ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲባራ ፉፋ (1ኛ ተከሳሽ)
አቶ ይላቅ አወቀ (4ኛ ተከሳሽ)
አቶ አበላ ግዛው (5ኛ ተከሳሽ)
አቶ ይልቃል የኔሰው (9ኛ ተከሳሽ)
የኛ ፔትሮሊየም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (10ኛ ተከሳሽ)
ቀደም ሲል ለተቋማት ያለአግባብ የነዳጅ ግዥ ፈቃድ በመስጠት እና የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ በመንግሥት ላይ የከባድ ሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል በ13 ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ክስ ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ሦስተኛው የክስ ዝርዝር የኛ ፔትሮሊየም ድርጅት ከሕግ አግባብ ውጭ የነዳጅ አከፋፋይነት ፈቃድ እንዲያገኝ በማድረግ በመንግሥት ላይ ከ21.3 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል የሚል ነበር።
የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቸርነት ሆርዶፋ የፈረሙበት እና ለፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሃና አርአያሥላሴ በግልባጭ እንዲያውቁት የተደረገው ይህ የክስ መቋረጥ ትዕዛዝ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርቧል። ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ትዕዛዝ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የአቶ ይልቃል የኔሰው እና የየኛ ፔትሮሊየም ጠበቃ የሆኑት አቶ ወንድማገኝ ጸጋዬ እንደገለጹት፣ ውሳኔው ለችሎት የቀረበው ቀደም ብሎ ከተሰጠው የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የችሎት ቀጠሮ በፊት በመሆኑ በውስጥ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎ ይታመናል።
ችሎቱ ትዕዛዙን ተቀብሎ ውሳኔ ሲያስተላልፍ በሕግ ጥላ ሥር የሚገኙት አቶ ይላቅ አወቀ፣ አቶ አበላ ግዛው እና አቶ ይልቃል የኔሰው የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ ነጻ እንደሚሆኑ ጠበቃው አረጋግጠዋል።
ይሁን እንጂ በመዝገቡ አንደኛ ተከሳሽ የሆኑት የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲባራ ፉፋ፣ ሦስተኛው ክሳቸው እንዲቋረጥላቸው ቢወሰንም በመዝገቡ ላይ የተካተቱ ሌሎች ተጨማሪ ክሶች ስላሉባቸው የፍርድ ቤት ሂደታቸው የሚቀጥል ይሆናል።
#fuelcrisis #corruptioncase #ethiopiancourt #justice #ministryofjustice #legalnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 days ago