Logo
Getu Temesgen
የጠፋው ታዳጊ በሰላም ተገኘ

- ወላጆች ለልጆቻችሁ ጥንቃቄ አድርጉ
#ethiopia | ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የ11 ዓመት ዕድሜ ያለው ነብዩ ኤርሚያስ (ያቡ) የተባለ ታዳጊ በመጥፋቱ ወላጆች አስቸኳይ የፍለጋ ጥሪ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፣ ታዳጊው ምሽት ላይ በጣፎ አማኑኤል አካባቢ በሰላም መገኘቱ ተረጋግጧል።

የታዳጊው መጥፋትና መገኘት ሁኔታ እንደሚከተለው ነው፤ ልጃቸው ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ እየተመለሰ በነበረበት ወቅት ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ከመንገድ ላይ በመኪና ጭነውት ይሄዳሉ።

ጣፎ አማኑኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ፣ ግለሰቦቹ ታዳጊውን መኪና ውስጥ ትተውት ቀጣይ ወዴት እንደሚወስዱት ለመመካከር ከባለማጠናከሪያው ወርደው በነበረበት ወቅት፣ ታዳጊው ምቹ አጋጣሚ አግኝቶ ከመኪናው ውስጥ በማምለጥ ሊሰወር ችሏል።

በመቀጠልም በአካባቢው የነበሩ ደግ አዋቂ ሰዎች ታዳጊውን ያገኙት ሲሆን፣ እርሱም መጥፋቱን ገልጾ የአባቱን ስልክ ቁጥር ይሰጣቸዋል።

በሰዎቹ ትብብር ለአባትየው በተደረገው የስልክ ጥሪ መሠረት ወላጆች ታዳጊው ወዳለበት ቦታ በመሄድ ልጃቸውን በሰላም ተረክበዋል።

ወላጆች ቀደም ሲል የታዳጊውን መጥፋት ለየካ አባዶ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቀው ስለነበር፣ አሁን መገኘቱንም ለሕግ አስከባሪው አካል በድጋሚ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

በዚህ አስጨናቂ ወቅት ታዳጊው እንዲገኝ መረጃ በማጋራት፣ በማፈላለግ እንዲሁም የሕግ አካላትን ጨምሮ አጋርነታቸውን ላሳዩ ወገኖች ሁሉ ወላጆች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ወላጆች በሙሉ ለልጆቻቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

https://www.facebook.com/s...
#የህጻናትደህንነት #ፖሊስ #የካአባዶ #ጣፎ #ጥንቃቄ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.