የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ የጣለውን ጥብቅ የጉዞ እገዳ አደሰ
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ኮመንዌልዝ እና ልማት ቢሮ (FCDO) በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የፀጥታ ስጋት ተከትሎ ለዜጎቹ ያወጣውን ጥብቅ የጉዞ ማማከርያ መመሪያ አድሷል ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ ስር የሰደደ አለመረጋጋት እና ግጭቶች ባሉባቸው በርካታ ክልሎችና የድንበር ቀጠናዎች ላይ "በፍጹም ጉዞ እንዳይደረግ" የሚለውን ቀጣይነት ያለው እገዳ በድጋሚ አሳስቧል።
1. ሙሉ በሙሉ ጉዞ የተከለከለባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች (All Travel)
የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ወቅታዊ መመሪያ መሰረት በከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ምክንያት በሦስት ዋና ዋና ክልሎች ማለትም በትግራይ በአማራ እና በጋምቤላ ክልሎች ላይ ሙሉ በሙሉ የጉዞ ክልከላ ጥሏል።
ከእነዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ የድንበር ቀጠናዎች ላይ ጥብቅ እገዳዎች ተጥለዋል፦
የሱዳን ድንበር፦ከድንበሩ በ20 ኪ.ሜ ክልል ውስጥ (ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ መተከል እና ማኦ ኮሞ ልዩ ዞንን ጨምሮ)
የደቡብ ሱዳን እና የኬንያ ድንበሮች፦ከድንበሩ በ10 ኪ.ሜ ክልል ውስጥ (የቱርካና ሃይቅ ዳርቻዎችን ጨምሮ)
የሶማሊያ ድንበር (በሶማሌ ክልል)
ከድንበሩ በ100 ኪ.ሜ ርቀት ውስጥ (ከጅጅጋ-ወጃሌ ዋና መንገድ እና ከወጃሌ መሻገሪያ ውጭ) በፍጹም ጉዞ እንዳይደረግ አሳስቧል።
በኦሮሚያ ክልልም ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋን ጨምሮ በምዕራብ ሸዋ እና ሰሜን ሸዋ የሚገኙ አካባቢዎች በዚሁ የ"በፍጹም ጉዞ አታድርጉ" ቀጠና ውስጥ ተካትተዋል።
2. "አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር" ጉዞ እንዳይደረግባቸው የተመከሩ አካባቢዎች (All but Essential)
የኤርትራ ድንበርን ተከትለው በሚገኙ ከ10 እስከ 15 ኪ.ሜ ርቀቶች ላይ በአብዛኛው የኦሮሚያ ምስራቅ ሸዋ ዞን (ከአዲስ አበባ-አዳማ የፍጥነት መንገድ እና ወደ ሐዋሳ ከሚወስደው መንገድ ውጭ) እንዲሁም በሶማሌ ክልል የሚገኙት ሲቲ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ሻቤሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ተጓዦች በጣም አስገዳጅ ጉዳይ ካልገጠማቸው በስተቀር መሄድ እንደሌለባቸው ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ አያይዞ እንዳሳወቀው በአዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ሰራተኞች የጉዞ እገዳ በተጣለባቸው በእነዚህ የሀገሪቱ ክፍሎች ተገኝተው ለዜጎቻቸው በአካል ምንም ዓይነት የቆንስላ ድጋፍ ማድረግ አይችሉም።
ይሁን እንጂ ዜጎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋልን የመሰሉ ከባድ ድንገተኛ አደጋዎች ሲገጥሟቸው በአዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው ኤምባሲ በኩል በስልክ ጥሪ ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ተጓዦች ወደ ሀገሪቱ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ሙሉ የጉዞ ዋስትና (Travel Insurance) ሊኖራቸው እንደሚገባም መመሪያው አሳስቧል።

2 months ago