Logo
SeledaPost
“ምርጫው በሰላም መጠናቀቁ በጎ ቢሆንም መዋቅራዊ ጥሰቶች ነበሩበት” - ኢዜማ

​የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደውን 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማዊ መግለጫ አውጥቷል።

ፓርቲው ምርጫው ከሞላ ጎደል በሰላም መጠናቀቁን፣ ከፍተኛ የመራጭ ቁጥር መመዝገቡንና የኦንላይን አሰራር መጀመሩን እንደ በጎ ጅምር ወስዷል።

​በሌላ በኩል፣ በሂደቱ ላይ የታዩ በርካታ መዋቅራዊ ተግዳሮቶችንም ወቅሷል። ገዢው ፓርቲ የመንግሥት የልማት ፕሮግራሞችን እና የሚዲያ አቅምን ለምርጫ ቅስቀሳ መጠቀሙን፣ እንዲሁም የካድሬዎችና የጸጥታ አካላት በምርጫ ጣቢያዎች ጣልቃ በመግባት በመራጮችና በተቃዋሚ ታዛቢዎች ላይ ጫና ማድረጋቸውን ገልጿል።

​በተጨማሪም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈጻሚዎች ገለልተኝነት ማጣት፣ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሟላ ታዛቢ አለማሰማራት እና የሲቪክ ማኅበራት ደካማ ተሳትፎ በምርጫው ላይ ክፍተት መፍጠራቸውን አብራርቷል።

ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም የራሳቸውን ፍላጎት አስቀድመው ሂደቱን ሲያጣጥሉ እንደነበር ጠቁሟል።

​ኢዜማ በስተመጨረሻም፣ ያሉትን ውስብስብ ችግሮች ተጋፍጦ የተሻለ ስኬት ማስመዝገቡን ጠቅሶ፣ ሥልጣን መያዝ የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ብቻ በመሆኑ በቀጣይም ለዲሞክራሲ ግንባታ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታውቋል።

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.