7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአማራ ክልል ሕዝብ እና አመራሩ ወደ አዲስ የመንቃት ምዕራፍ የተሻገሩበት የልዩ ዘመን መክፈቻ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*******************
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ የከፍተኛ አመራሮች የግምገማ መድረክ መካሄዱን እና በመድረኩ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አፈጻጸም እና ስትራቴጂካዊ ውጤቶች በጥልቀት መገምገሙን ገልጸዋል።
ይህ ምርጫ የክልሉ ሕዝብ እና አመራር ከጠላት መጠነ ሰፊ ሴራዎች ከፍ ብለው በመራመድ፣ ለክልሉ ዘላቂ ልማት እና ሰላም በጠራ መስመር እና በማይናወጥ አንድነት በመቆም የማይሻር ገድል የፈጸሙበት ነው ብለዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “ሕዝባችን በዚህ ምርጫ ያሳየው ወደር የለሽ የሰላም ቁርጠኝነት እና የዴሞክራሲ ብስለት፤ በክልሉ ላይ በባዕዳን እና በባንዳዎች የተጋረጡ የጥፋት ማነቆዎችን ሙሉ በሙሉ እንዲቀለበሱ አስችሏል” ሲሉ ገልጸዋል።
በቀጣይም የክልሉን እምቅ አቅም ለመጠቀም ሰላምን በዘላቂነት ማጽናት፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች በቁርጠኝነት መመለስ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ በግምገማው የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን አረጋግጠዋል።
#ethiopia #ebc #ethiopiaprevails

15 hours ago