Logo
Getu Temesgen
አዲስ ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርድ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር አዲስ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ በጋራ ይፋ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ይህ አዲስ የቪዛ ካርድ ደንበኞች ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት በሚጓዙበት ወቅት የገንዘብ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመፈጸም የሚያስችላቸው ሲሆን፣ ካርዱን በሚጠቀሙበት ጊዜም የሸባ ማይልስ ማበረታቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

አገልግሎቱን ለማግኘት ግን የሁለቱም ተቋማት ማለትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኛ መሆን ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እንደገለጹት፣ የአሁኑ ዘመን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በስፋት የሚፈልግ በመሆኑ ይህ ይፋ የተደረገው ዓለም አቀፍ ካርድ የባንኩን ደንበኞች የውጭ ሀገር የንግድና የገንዘብ ዝውውር በእጅጉ የሚያቀላጥፍ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ በበኩላቸው፣ አየር መንገዱ የደንበኞቹን የአገልግሎት እርካታ ለማሳደግና አሠራሩን ዘመናዊ ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ አዲሱ የክፍያ ካርድ የሁለቱንም አንጋፋ ተቋማት ደንበኞች በእጅጉ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማብራራታቸውን አሚኮ በዘገባው አስፍሯል።
#የኢትዮጵያንግድባንክ #የኢትዮጵያአየርመንገድ #ቪዛካርድ #የዲጂታልክፍያ #የባንክአገልግሎት #የአየርጉዞ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

21 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.