የንፁሃን ደም መፍሰስ ይብቃ፡ ለዘላቂ ሰላም በጋራ እንምከር!
#ethiopia | በሀገራች የዜጎች ሞት ስፍራ አየቀያየረ ቀጥሏል።ዛሬ ደግሞ በተደጋጋሚ ሞት እየተሰማበት ባለው በምስራቅ አርሲ ዞን በንፁሃን በኦርቶዶክስ ከርስትያን ወገኖቻችን ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ መደረጉን፣ ቤተ ክርስቲያንና የአማኞች መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ከሚዲያዎች ዘገባ መረዳት ችያለሁ። መሰል ጥቃቶች ራስን በተጠቂዎች ቦታ አድርገን ካየን በእጅጉ ልብን በኃዘን ይሰብራል።
የንፁሃን ደም ያለአግባብ መፍሰስ እና የዜጎች መገደል በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል።ግና እንዴትና መቼ? እንዴትስ ላለፉት ዓመታት በንጹሃን ዜጎችና በቤተ እምነቶች(መስጊድና ቤተክርስቲያን) ላይ የደረሱት ጥቃቶች የአንዱ ፈጻሚዎች እንኳ በህግ ቁጥጥር ስር ማዋልና ተጠያቂ ማድረግ ሳይቻል ቀረ? ከድርጊቱ በላይ መደጋገሙ፣ከመደጋገሙ በላይ ፈጻሚዎቹ ሁሌም ያልታወቁ እየተባሉ መፍትሄ ማምጣት አለመቻል አደገኛ ነው።
ዘላቂ መፍትሄ ይገኝ ዘንድ ቆም ብሎ ማሰብ፣በ ስሜት ተጽዕኖ ስር ከመውደቅ በራቀ መልኩ ነገሮችን መመርመር፣መምከርና በጋራ መፍትሄ መፈለግ ግድ ይላል።
ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ነፍስ እንዲህ መርከሱ እጅግ አደገኛ ነገር ነው።አላህ በቁርኣን እንዲህ ይለናል።
مِنۡ أَجۡلِ ذَٰلِكَ كَتَبۡنَا عَلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ أَنَّهُۥ مَن قَتَلَ نَفۡسَۢا بِغَيۡرِ نَفۡسٍ أَوۡ فَسَادٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ ٱلنَّاسَ جَمِيعٗا وَمَنۡ أَحۡيَاهَا فَكَأَنَّمَآ أَحۡيَا ٱلنَّاسَ جَمِيعٗاۚ وَلَقَدۡ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُنَا بِٱلۡبَيِّنَٰتِ ثُمَّ إِنَّ كَثِيرٗا مِّنۡهُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ فِي ٱلۡأَرۡضِ لَمُسۡرِفُونَ
— سورة المائدة (5:32)
"በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን፡፡ መልክተኞቻችንም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጡዋቸው፡፡ ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው፡፡"
— አል-ማኢዳህ (5:32)
ይህ ቁርኣናዊ መለኮታዊ መመሪያ የሰው ልጅ ሕይወት ነፍስ በማለት በመጥራት ያለ ምንም የዘር፣ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት ፍጹም የተከበረና የማይደፈር መሆኑን ያረጋግጣል።
በአንቀጹ መሠረት አንዲትን ንጹሕ ነፍስ ያለ አግባብ መቅጠፍ መላውን የሰውን ዘር እንደ ማጥፋት የሚቆጠር እጅግ ከባድ ወንጀል ሲሆን፣ በተቃራኒው ደግሞ አንዲትን ነፍስ ከአደጋ መታደግና ማዳን መላውን የሰው ልጅ ሕይወት እንደ ማኖር የሚቆጠር ታላቅ ሰብአዊ በጎነት ነው።
እንደ ዜጋ ማድረግ የምንችለው ለሟች ቤተሰቦችና ወገኖቻች መጽናናትን መመኘት ብቻ በመሆኑ እያዘንኩ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ።
ህዝባችንና ሀገራችንን ከጥፋትና ከእልቂት ጠብቅልን።አላህ ሆይ! እውነቱ እንዲወጣ፣ የንጹዃን ደምም አፍሳሾች መቀጣጫ ይሆኑ ዘንድ የእጃቸውን እንዲያገኙ አድርግልን።አላህ በቃችሁ በለን!
ኡዝታዝ አህመዲን ጀበል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago