የኢድ አል አድሀ በዓልን አስመልክቶ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን ለመከላከል ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መጪውን 1447ኛውን የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል መቋረጥ ለመቀነስ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በበዓላት ቀናት የህዝቡ የኃይል ፍላጎትና አጠቃቀም በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምር በመሆኑ፣ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ ላይ የሚፈጠረውን ከፍተኛ ጫና ለመቋቋም ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።
ከእነዚህ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መካከል የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመሮች ፍተሻ ማካሄድ፣ የረገቡ ገመዶችን መወጠር፣ የእንጨት ምሰሶዎችን በኮንክሪት መተካት እንዲሁም ከፍተኛ ጫና ያለባቸውን ትራንስፎርመሮች አቅም ማሳደግና አዳዲስ አጋዥ ትራንስፎርመሮችን መትከል በዋናነት ይጠቀሳሉ።
በዚህም መሠረት በተቋሙ ሥር በሚገኙ ነባር መሰረተ ልማቶች ላይ ሙሉ የቅድመ መከላከል ፍተሻ የተደረገ ሲሆን፣ ለኃይል መቆራረጥ ምክንያት ይሆናሉ ተብለው ከተለዩት ችግሮች መካከል በዋናው ኔትዎርክ 80 በመቶ እንዲሁም በትራንስፎርመር ላይ የነበሩትን 70 በመቶ ችግሮች መቅረፍ ተችሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በዋዜማውና በበዓሉ ዕለት አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት፣ የኃይል መቆራረጥ ሲያጋጥምም አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ የአስቸኳይ ጥገና ግብረ-ኃይል በሁሉም መዋቅሮች ተደራጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል።
በዕለቱ በተመረጡ ማዕከላት የካርድ መሙላት አገልግሎት የሚሰጥ ቢሆንም፣ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች የያዙት የኃይል መጠን መኖሩን አስቀድመው በማረጋገጥ በዓሉ ከመድረሱ በፊት እንዲሞሉ ተቋሙ ጥሪ አቅርቧል።
በመጨረሻም ደንበኞች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ጥቆማዎችና መረጃዎች በ905 ወይም በ904 የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ስልክ ቁጥሮች፣ በተቋሙ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ወይም በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በኩል ማሳወቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #አረፋ #የኤሌክትሪክኃይል #አገልግሎት #ኢድአልአድሀ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago