Logo
Getu Temesgen
በፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ የበላይነት ጊዜ የየትኛው ክለብ ነው?
#ethiopia | ማንቺስተር ዩናይትድ 1995-2001

የሰር አሌክስ ፌርጉሰን የመጀመሪያው ምርጡ ቡድን ነው።ቀያይ ሰይጣናቱ ከመጀመሪያ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎቻቸው ሰባቱን ያሳኩበት ነው።የ1998-99 የሶስትዮሽ ዋንጫን ያሳኩበት ውድድር አመት ደግሞ በምርጥነቱ የሚነሳው ነው።ግማሽ የሚሆነው የቡድን ስብስብ የተገኘው ደግሞ "ከclass of 92" ነው።እንደ ዴቪድ ቤካም ጋሪ እና ፊል ኔቭል ኒክ በት ሪያን ጊግስ እና ፖል ስኮልስ ያሉት ማለት ነው።
ኤሪክ ካንቶና ፒተር ሽማይክል ሮይ ኪን አንዲ ኮል እና ድዋይት ዮርክ በወቅቱ በቡድኑ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ክዋክብት ተጫዋቾች ናቸው።

አርሰናል 2001-2004

የአርሰን ቬንገር አርሰናል የሰር አሌክስ ቡድንን በወጥነት ለሊጉ ዋንጫ ክብር መፎካከር የቻለ የመጀመሪያው ቡድን ነው።በ1997-98 እና 2001-02 የሁለትዮሽ ዋንጫን ክብር ያሳካ ሲሆን በ2003-04 ደግሞ "Invincible" ሆኖ ባለ ክብር ሆኗል።

ከ1999-2005 ስምንት ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።በዚህ ቡድን ውስጥ ፈረንሳውያኑ ኮከቦች ቲዬሪ ሆነሪ ፖትሪክ ቪዬራ እና ሮበርት ፒሬዝ ሆላንዳዊው ጥበበኛ ዴኒስ ቤርካምፕ እንግሊዛውያኑ ተከላካዮች አሽሊ ኮል እና ሶል ካምቤል ከምርጦቹ መካከል ነበሩ።

ቼልሲ 2004-2007

ጆዜ ሞውሪንሆ በሰማያዊዮቹ ቤት በ2004 ከመጡ በኋላ የራሳቸውን ትልቁን አሻራ ማኖር የቻሉት በፍጥነት ነበር።

ራሳቸውን "The Special One" በማለት ለእንግሊዝ ሚዲያ ያስተዋወቁበት መንገድ ትልቁ የመነጋገሪያ ርዕስም ነበር።በመጀመሪያው ዙር ቆይታቸው ሁለት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ሲያነሱ በሶስተኛ የውድድር ዘመን የክለቡ ቆይታቸው ቡድናቸው ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በመጀመሪያ የውድድር አመት ቆይታቸው የሊጉን ዋንጫ ሲያሳኩ እስካሁን ያልተሰበሩ በርካታ ሪከርዶችን በመያዝ ነው።

እንግሊዛውያኑ ፍራንክ ላምፓርድ ጆን ቴሪ እና ጆ ኮል ግብ ጠባቂው ፔተር ቼክ የተከላካይ አማካዩ ክሎድ ማኬሌሌ እና አጥቂው ዲዲዬ ድሮግባ ከወርቃማው ቡድን ተጫዋቾች መካከል ዋነኞቹ ነበሩ።

ማንቺስተር ዩናይትድ ከ2006-2011

የፌርጉሰን ሁለተኛው ምርጡ ቡድን ነው።ለሶስት ተከታታይ የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከተሳነው በኋላም በአምስት አመት ውስጥ ለአራት ጊዜያት ያህል ባለ ክብር የሆነበት ነው።በ2007-08 ደግሞ የሻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ አሳክቷል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ዌይን ሩኒ ግብ ጠባቂው ኤድዊን ቫንደርሳር አይረሴዎቹ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች ነበሩ።

ማንቺስተር ሲቲ ከ2017-2024

በስተመጨረሻ የአሁኑን የጋርዲዮላ ቡድን እናገኛለን።በቶፕ ዲቪዥን ተከታታይ አራት የሊግ ክብሮችን በማሳካት የመጀመሪያው ቡድን ነው።በ2017- 18 100 ነጥቦችን በቀጣይ አመት ደግሞ 98 መሰብሰብ ችሏል። በ2022-23 የውድድር ዘመን የሶስትዮሽ ዋንጫን ክብር አሳክቷል። በዚህ ጊዜ የሲቲን የበላይነት ለመፈተን ጥረት ያደረገው ቡድን የየርገን ክሎፕ ሊቨርፑል ብቻ ነው ብሎ ማንሳት ይቻላል።

ኬቨን ዴብሩይነ ኤደርሰን በርናንዶ ሲልቫ ካይል ዎከር በልዩነት በዚህ ስኬታማ ጊዜ ውስጥ ስማቸው በትልቁ የሚነሳ ተጫዋቾች ናቸው።

(በሳምሶን አበበ)

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.