Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ቲክ ቶክ ከኢትዮጵያ 1,820,961 ቪዲዮዎችን ማጥፋቱን ገለፀ፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ተቋም የሆነው ቲክ ቶክ የ2025 አራተኛ ሩብ አመት ሪፖርቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም ደንብ በመተላለፍ ያጠፋቸውን ቪዲዮዎች ብዛት ገልጿል፡፡ በመላው አለም ከኦክቶበር ወር እስከ ዲሴምበር ወር ድረስ ከ175 ሚሊዮን በላይ ቪዲዮዎችን ማጥፋቱን የጠቀሰው ቲክ ቶክ ከዚህ ውስጥ 1,820,961 ያህሉ የኢትዮጵያዊያን መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው የ3ተኛው ሩብ አመት ሪፖርት ላይ ከኢትዮጵያ ከ3 ሚሊዮን በላይ ቪዲዮዎችን ማጥፋቱን ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ዛሬ ይፋ በሆነው የ4ተኛው ሩብ አመት ሪፖርቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ቪዲዮ ያጠፋው ከአሜሪካ መሆኑን ገልፆ ብዛታቸውም ከ10 ሚሊዮን እንደሚበልጥ አስረድቷል፡፡ ከኢትዮጵየ ጎረቤት አገራት መካከል ከኬንያ 820 ሺህ ቪዲዮ፣ ከሱዳን 1 ነጥብ አራት ሚሊዮንና ከሱማሊያ 973 ሺህ ቪዲዮ ማጥፋቱን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡

16 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.