አሉታዊ ትርክቶችን የተሻገረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአምስቱ ምሰሶዎች ስኬት
*************************
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት በሚያከናውናቸው መጠነ ሰፊ የልማት ሥራዎች ላይ አልፎ አልፎ "ብልጭልጭ ጉዳዮች ላይ ብቻ ያተኮረ" የሚል ትችት ይሰማል።
ይሁን እንጂ መንግሥት ተግባራዊ እያደረገው ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ብዝኃ-ዘርፍን መሠረት ያደረገ እና ሁሉንም ቁልፍ የኢኮኖሚ ሞተሮች በእኩል ደረጃ በማልማት ላይ የተመሠረተ ስትራቴጂ ነው።
ይህ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱን ዘርፍ ብቻ ነጥሎ የሚያለማ ሳይሆን ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ዲጂታል ኢኮኖሚን በእኩል ደረጃ የሚያንቀሳቅስ መሆኑ በተግባር እየታየ ይገኛል።
ይህ መዋቅራዊ ማሻሻያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሥርዓት ከፍጆታ ወደ ምርት፣ ከአስመጪነት ወደ ላኪነት እና ከመንግሥት-መር ወደ ግል ዘርፍ መሪነት የሚያሻግር ጠንካራ መሠረት እየጣለ ይገኛል።
በግብርናው ዘርፍ የተመዘገበው ታሪካዊው የስንዴ አብዮት ኢትዮጵያን ወደ ላኪነት እያሸጋገረ ሲሆን፣ በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ የስንዴ ምርት አቅም 305 ሚሊዮን ኩንታል መድረሱ ይህንኑ ያረጋግጣል።
በሌላ በኩል፣ “ኢትዮጵያ ታምርት” በተሰኘው ሀገራዊ ንቅናቄ አማካኝነት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 58 በመቶ የተኪ ምርት ድርሻ ላይ ደርሷል።
የዚህ ማሳያ የሚሆነው በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄው ምርት አቁመው የነበሩ 993 ፋብሪካዎች ዳግም ወደ ምርት መግባታቸው ነው።
ቀደም ሲል ትኩረት ሳይሰጣቸው የቆዩት የኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶች አሁን እሴት ተጨምሮባቸው የኢኮኖሚው አዲስ የጀርባ አጥንት መሆን ችለዋል።
በማዕድን ዘርፉ በተወሰዱት የሕግ እና አሠራር ማሻሻያዎች የድንጋይ ከሰል የሀገር ውስጥ ገበያ ድርሻ በ2010 ከነበረበት 17 በመቶ በ2017 ወደ 75 በመቶ ማደግ ችሏል። ወርቅም የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት ከቡና ልቆ የተገኘው በዚሁ ማሻሻያ ነው።
በቱሪዝም ዘርፍም የ“ገበታ” ፕሮጀክቶች አዳዲስ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን በመፍጠርና የቱሪስት ገበያውን በማስፋት ለውጥ እያመጡ ይገኛሉ።
በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 9 ወራት ብቻ 1.2 ሚሊዮን የውጭ ቱሪስቶችን በመሳብ ከ2.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ፖሊሲው ውጤማነት ማረጋገጫ ነው።
በቴክኖሎጂውና በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ረገድ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂ በስኬት ተጠናቅቆ ቦታውን ለ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂ አስረክቧል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ የፋይናንስ ተደራሽነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ፣ እስከ መጋቢት 2018 ድረስ የተከፈቱ ዲጂታል አካውንቶችን ቁጥር 257.8 ሚሊዮን ማድረስ ተችሏል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለሀገራዊ ኢኮኖሚው የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም እንደ “መላ” ያሉ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን የሚረዱ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ሥርዓቶችን በማልማት ኢትዮጵያን በአፍሪካ መሪ አድርጓታል።
ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) በጤናው ዘርፍም እያመጣው ያለው እመርታ በአፍሪካ ሕብረት ጭምር ማረጋገጫ የተሰጠው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕብረቱ ሹመት ያገኙበት ነው።
በአጠቃላይ በእነዚህ አምስቱ ምሰሶዎች የተገኙ ስኬቶች ሀገራችን ከዚህ ቀደም ይገጥማት የነበረውን የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ለመቅረፍ ትልቅ አቅም ፈጥረዋል።
የሥራ አጥነት ችግርን ከመቅረፍ አኳያ፣ እነዚህ ንቅናቄዎች በ2018 በሦስተኛው መቶ ቀናት ውስጥ ብቻ ከ96 ሺህ በላይ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ለዜጎች ተጠቃሚነት የላቀ ሚና ተጫውተዋል።
ባለፉት 8 ዓመታት ኢኮኖሚው በአማካይ በ7.5 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ በ2018 ደግሞ የ10.2 በመቶ ድርብ አሀዝ ዕድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል።
ይህ ሁሉ ሀገራችን በትክክለኛው የለውጥ እና የዘላቂ ብልጽግና ጎዳና ላይ መሆኗን በተጨባጭ የሚያስረግጥ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #economy #homegrowneconomicreform #ebc

16 days ago