(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ ነዳጅ ማደያዎች የሳይበር ጥቃት እንደደረሰባቸው ተዘገበ፡፡ ሲኤንኤን እንዳቀረበው ዘገባ በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የሚገኙ የነዳጅ መቆጣጠሪያ ስርአቶች ላይ የሳይበር ጥቃት ተፈፅሟል፡፡ ጥቃቱ ያነጣጠረው በአውቶማቲክ የነዳጅ ማጠራቀሚያ መለኪያ ስርአቶች ላይ እንደሆነ የጠቀሰው ዘገባው በዚህም እነዚህ ሲስተሞች በኦንላይን ካለፓስወርድ እንዲሰሩ መደረጋቸውን አስረድቷል፡፡
ጥቃት ፈፃሚዎቹ በአንዳንድ ነዳጅ ማደያዎች ላይ በስክሪን ላይ የሚታየውን የንባብ መጠን እስከመቀየር መድረሳቸውንም ገልጿል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ምንጮቹን የጠቀሰው ዘገባው በዚህ ጥቃት በማከማቻ ውስጥ በሚገኝ ነዳጅ መጠን ላይ ምንም ችግር አለመከሰቱን አስታውቆ ነገር ግን ከፍተኛ የደህንነት ስጋትን የሚፈጥር መሆኑን አስረድቷል፡፡
እንዲህ አይነት ጥቃቶች የነዳጅ ፍሰትን ለመደበቅ የሚያስችሉ በመሆናቸው በሰውና በንብረት ላይ አደጋ ሊያደርሱ እንደሚችሉም አሳስቧል፡፡ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረጉ ያሉ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ለዜና አውታሩ ሲናገሩ ከዚህ ጥቃት በስተጀርባ ኢራን ልትኖርበት እንደምትችል አስታውቋል፡፡

1 month ago