Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) አረብ ሊግ በኢትዮጵያና በሱዳን ጉዳይ ተወያየ፡፡ የአረብ ሊግ ትላንት በካይሮ ባከናወነው አስቸኳይ ስብሰባ ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ባቀረበችው ክስ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡ ይህ ስብሰባ ሊከናወን የቻለው በካርቱም አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ላይ ባለፈው ሳምንት የደረሰውን የድሮን ጥቃት ተከትሎ ሲሆን ሱዳን በጥቃቱ የኢትዮጵያና የዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ እጅ እንዳለበት በመግለፅ ስሞታ ማቅረቧ ይታወሳል፡፡

እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኙትን አምባሳደሯን መጥራቷም አይዘነጋም፡፡ የሱዳን መንግስት ሜይ 6 ቀን ለአረብ ሊግ በላከው ደብዳቤ ጥቃቱን በተመለከተ በውጭ ጉዳይ ደረጃ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጥያቄ ማቅረቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ጥያቄው ተቀባይነት ቢያገኝም ስብሰባው ግን በቋሚ ተወካዮች ደረጃ እንዲከናወን በተወሰነለት መሰረት ትላንት ይህ ስብሰባ ሊደረግ ችሏል፡፡ ስብሰባውን በሊቀመንበርነት የመሩት የባህሬን የአረብ ሊግ ቋሚ ተወካይ ፋውዚያ ቢንት አብዱላሂ ዛናል ሲሆኑ ባደረጉት ንግግር ይህ ውዝግብ የሱዳንን ሉአላዊነት አንድነትና መረጋጋት በሚጠብቅ መልኩ ይፈታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ጨምረውም የሱዳን መረጋጋት በአረብ ሊግ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ውዝግብ እንዳይባባስና በቀጠናው ደህንነት ላይ ተፅእኖ እንዳፈጥር በጥንቃቄ መያዝ እንዳለበለት በመግለፅም ጉዳዩን አቃለውታል፡፡ ነገር ግን በሊጉ የሱዳን ተወካይ የሆኑት ኢማድ አዳዊ ‹‹ከኢትዮጵያ በኩል ተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈፀመብን ነው›› በማለት ቢናገሩም ስብሰባው ያለምንም ውሳኔ ሀሳብ መጠናቀቁን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

24 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.