ማንቼስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ36ኛ ሳምንት መርሐግብር ማንቼስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በኢትሃድ በተደረገው ጨዋታ የውሃ ሰማያዊዎቹን ግቦች ዶኩ፣ ሀላንድ እና ማርሙሽ በ2ኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ነጥቡን 74 በማድረስ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ችሏል፡፡
ቀደም ሲል በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ከሰንድርላንድ 0 ለ 0፣ ሊቨርፑል ከቼልሲ 1 ለ 1 አቻ ሲለያዩ፥ ብራይተን ወልቭስን 3 ለ 0 እንዲሁም በርንማውዝ ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

3 months ago