Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የስለላ (የመረጃ) ተቋማት አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ካሜኔይ ከሌሎች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በመሆን የኢራንን የጦርነት ስትራቴጂ በመቅረጽ እና በመምራት ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አረጋግጠናል አሉ። ይህንኑ መረጃ ለመስሪያ ቤቱ ቅርበት ያላቸውን በርካታ ባለስልጣናት ጠቅሶ ሲኤንኤን ዘግቦታል።

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ አባታቸውን በገደለው ተመሳሳይ ጥቃት ሞጅታባ ካሜኔይ ጉዳት ከደረሰባቸው ጊዜ አንስቶ፣ አሜሪካ የት እንደሚገኙ በዓይን አይታ ለማረጋገጥ አልቻለችም። መሪው ከጥቃቱ በኋላ በአደባባይ ታይተው አያውቁም።

በአሁኑ ወቅት መሪው ከእይታ ርቀው በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ፊታቸው፣ እጃቸው፣ ገላቸው እና አንደኛው እግራቸው ላይ ለደረሰባቸው ከባድ የእሳት ቃጠሎ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ምንጮቹ አክለው አብራርተዋል። በከባድ የህክምና ክትትል ውስጥ ሆነውም የሀገሪቱን የጦርነት አቅጣጫ በመወሰኑ ሂደት ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆናቸውን የአሜሪካ የስለላ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ባለፈው ኤፕሪል 29፣ 2026 በቴህራን በመንግስት በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ አንዲት ሴት የጠቅላይ መሪውን የሞጅታባ ካሜኔይን ፎቶግራፍ ይዛ ስታሳይ የሚያሳይ ምስል መውጣቱ ይታወሳል።

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.