ባለፉት 9 ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 366 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
********************
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)፤ ባለፉት 9 ወራት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በዚህም በገጠርና በከተማ በተገነቡ 3 ሺህ 278 የመጠጥ ውሃ ተቋማት 2.7 ሚሊዮን የኅብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ህዝብ ቁጥር ከነበረበት 79.5 ሚሊዮን ወደ 82.3 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ገልጸዋል።
በኢነርጂ ዘርፍም ከተለያዩ የኃይል ምንጮች በ9 ወራት 1 ሺህ 669 ሜጋ ዋት በማመንጨት፣ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅምን ወደ 9 ሺህ 579 ሜጋ ዋት ማሳደግ ተችሏል ብለዋል ሚኒስትሩ።
ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት 9 ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 314 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ፣ 365.9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት ከዕቅድ በላይ ስኬት መመዝገቡን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
የምክር ቤቱ አባላት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በንፁህ መጠጥ ውሃና በኢነርጂ ዘርፍ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ሥራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
አባላቱ አክለውም የጎርፍ ተጋላጭነትን በመቀነስ፣ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ በማድረግና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ቀጣይነት በማረጋገጥ ረገድ ሚኒስቴሩ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ይበልጥ ማሳደግ እንዳለበት ጠቁመዋል።
በአባዲ ወይናይ
#ethiopia #water #energy #ebc

3 months ago