Logo
EBC
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ጦርነት ሊያበቃ ነው? አዲሱ ስምምነት ምን ይዟል?
********************

ኢራን ከአሜሪካ የቀረበላትን አዲስ የውሳኔ ሃሳብ እየመረመረች መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን፣ ሁለቱ ወገኖች በባህረ ሰላጤው ያለውን ጦርነት በይፋ ለማቆም በሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ላይ ለመስማማት መቃረባቸው ተሰምቷል።

የፓኪስታን እና ሌሎች ከሽምግልና ሂደቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት፣ ስምምነቱ ጦርነቱን የሚገታ ባለ 14 ነጥብ የውሳኔ ሃሳብ የያዘ ነው።

ይህ የአንድ ገጽ ሰነድ እንደ የኑክሌር መርሃ ግብር ያሉ ውስብስብ ጉዳዮችን ለጊዜው ወደ ጎን በመተው፣ ይልቁንም በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በኩል ያለውን የመርከብ ጉዞ መክፈት፣ በኢራን ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ማንሳት እና በቀጣይ ውይይቶች በኑክሌር መርሃ ግብሩ ላይ ገደቦችን ስለማድረግ በሚሉ ነጥቦች ላይ ትኩረት ያደርጋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ ሀገራቸው አቋሟን በሽምግልናው ግንባር ቀደም ሚና ባላት ፓኪስታን በኩል የምታሳውቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ባሰፈሩት ጽሑፍ "ኢራን በተስማማንበት ጉዳይ ላይ ከተስማማች" ጦርነቱ ሊያበቃ እንደሚችል የገለጹ ቢሆንም፣ ስምምነት ለመፈረም ፊት ለፊት ለመገናኘት ግን ገና መሆኑን ለኒውዮርክ ፖስት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የአሜሪካ ወታደራዊ አጋር የሆነችው እስራኤል ስለ ስምምነቱ መቃረብ መረጃው እንደሌላት ገልጻ፣ ለተጨማሪ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን አስታውቃለች።

በመሀመድ ፊጣሞ
#ebc #iran #usa #peacedeal #donaldtrump #gulfwar #worldpolitics

30 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.