እነዚህ ሳይወገዱ የትግራይ ህዝብ ሰላም አያገኝም - አቶ ጌታቸው ረዳ
አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ በተመለከተ በህወሓት አመራሮች ላይ ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረዋል።
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካ ቀንድ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው፣ "ቃንጫ መርዓት" የሚባለውን የህፃናት ጨዋታ እንደ ምሳሌ በመጥቀስ በክልሉ እየተከናወነ ያለው ድርጊት አሳዛኝ መሆኑን ገልጸዋል።
"ቃንጫ መርዓት የተባለ የህፃናት ጨዋታ፤ ህፃናት እንኳ ሲያድጉ የሚያቆሙትን እነዚህ የተወሰኑ ደናቁርት ግን ዛሬም እያላገጡ ደግመውታል” ሲሉ ገልፀዋል።
“እንሳቅ ወይስ እናልቅስ? እነዚህ ሳይወገዱ የትግራይ ህዝብ ሰላም አያገኝም" ሲሉ አቶ ጌታቸው በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በከፍተኛ ቁጭት ገልጸዋል።
ይህ የአቶ ጌታቸው ንግግር በክልሉ አመራሮች መካከል ያለውን ጥልቅ ልዩነት እና የፖለቲካ ሽኩቻ ይበልጥ የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል።
seledadotio

1 month ago