Logo
EBC
ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጣለ
***********

በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ ከኤቨርተን ጋር ሦስት አቻ ተለያይቷል፡፡በሂል ዲኪንሰን በተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ጄርሚ ዶኩ በባከነ ሰዓት ባስቆጠራት ግብ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡

ሲቲ በመጀመሪያው ግማሽ ጄርሚ ዶኩ ባስቆጠራት ግብ መምራት ቢችልም ውጤቱን ማስጠበቅ አልቻለም፡፡ በ2ኛው ግማሽ ተቀይሮ የገባው ቴርኖ ባሪ የኤቨርተንን ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር፣ ጃክ ፓትረክ ኦብሪን ተጨማሪውን ግብ አስቆጥሯል፡፡

ሃላንድ እና ጄርሚ ዶኩ በባከነ ሰዓት የማንችስተር ሲቲን ተጨማሪ ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ማንችስር ሲቲ ከአርሰናል ያለውን የስድስት ነጥብ ልዩነት ወደ ሦስት የሚያጠብበትን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት የቀረ ሲሆን የፕሪሚር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት ዕድሉም ከእጁ ወጥቷል፡፡

ሊጠናቀቅ የሦስት ጨዋታዎች ዕድሜ ብቻ በቀሩት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከ22 ዓመት በኋላ የሊጉን ዋንጫ የማሳካት ዕድሉም ሰፊ ሆኗል፡፡

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.