Logo
EBC
ከምኞት ወደ እውነት፦ የኢትዮጵያ አዲሱ የሉዓላዊነት ጉዞ በ21ኛው ክፍለ ዘመን
**************
የኢትዮጵያ ታሪካዊ የሉዓላዊነት ጽንሰ-ሀሳብ በአብዛኛው የተገነባው ዜጎቿ ሀገርን ለማዳን በጦር ሜዳ ላይ በከፈሉት ወደር የለሽ መስዋዕትነት እና ባፈሰሱት ደም ነው።

በደም የተጠበቀ ታሪካዊ ነጻነቷን በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ እና በአእምሮ በዳበረ የተሟላ ሉዓላዊነት ለማጽናት ታሪካዊ ጉዞ ላይ ትገኛለች፡፡

በ21ኛው ክፍለ ዘመን እውነተኛ ሉዓላዊነት ከድንበር ጥበቃ ባለፈ ከምግብ እና ከሌሎች የውጭ ጥገኝነት መላቀቅ መሆኑን በተግባር እያስመሰከረች ነው፡፡

በግብርናው ዘርፍ በየዓመቱ ለስንዴ ግዢ ይወጣ የነበረውን አንድ ቢሊዮን ዶላር በማስቀረት ራስን መቻል ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

በ"ሌማት ትሩፋት" እና በ"አረንጓዴ አሻራ" መርሐግብሮች የተመዘገቡ ስኬቶችም የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ብሔራዊ ክብርን ከፍ አድርገዋል፡፡

በኢንዱስትሪው ዘርፍ "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ወደ ሥራ የተመለሱ 993 ፋብሪካዎች የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን እያጠናከሩ ይገኛሉ፡፡

እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም ያሉ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች የኃይል ሉዓላዊነታችንን በማረጋገጥ የኢንዱስትሪውን ዕድገት እያፋጠኑ ነው፡፡

በቴክኖሎጂው ዘርፍ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ወጣቶችን በክህሎት በማስታጠቅ ቴክኖሎጂያዊ ጥገኝነትን ለማስቀረት ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክም የራሷን ትርክት በራሷ ለመጻፍ የጀመረችው ጉዞ የዚሁ የተሟላ ሉዓላዊነት ማሳያ ነው፡፡ ይህ ታሪካዊ ሽግግር ለነገው ትውልድ የምናወርሰው ታላቅ ሀገራዊ ቃል ኪዳን ነው፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ በአስተያየት መስጫ ውስጥ ያለውን ሊንክ ይጫኑ፡፡ 🔗

በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #sovereignty #economictransformation #digitalethiopia #ethiopiatamrit #greenlegacy

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.