Logo
Zehabesha
*በጣም ጠንከር ያላለ ፍራሽና የወገብ ህመም (በመረጃ ላይ የተመረኮዘ)*
የወገብ ክፍል ላይ የሚሰማ ህመም በብዙ ሰው ላይ የሚታይ ችግር ሲሆን መልካም እንቅልፍ ከህመሙ ለማገገም ጥሩ ሚና ይጫወታል።

መልካም እንቅልፍ ለማግኘት የምንተኛበት ፍራሽ ይሄ ነው የማይባል አስተዋጽኦ አለው።
ለሁሉም ሰው አንድ አይነት ፍራሽ ይሆናል ባይባልም፤ ከምርምር በተከታታይ የሚገኙ ውጤቶች እንደሚያሳዩት የምንተኛበት ፍራሽ መጠንከርና መላላት በጀርባ አጥንት አቀማመጥ ፣ በመኝታ ምቾትና በህመም መጠን ላይ አስተዋጽኦው የጎላ ነው።

መሆን ያለበት በእንቅልፍ ወቅት የጀርባ አጥንታችን ተስተካክሎና በተፈጥሮ ቅርፁ ተደግፎ እንዲቆይ ማስቻል ነው። ፍራሽ በጣም ለስላሳ ሲሆን ሰውነታችን በተለይ በዳሌ አካባቢ ያለው አካላችን ወደ ውስጥ ስለሚሰምጥ ያልተስተካከለ የአጥንት አቀማመጥ ይፈጥራል። በተቃራኒው ፍራሹ በጣም የደረቀ ሲሆን የጀርባ አጥንታችንን የተፈጥሮ ቅርፅ እንዳይዝ በማድረግ ምቾት ይነሳናል። ይህም በዳሌና በትከሻ አካባቢ ላይ ጫና ይፈጥራል ። ሁለቱም ሁኔታዎች ምቾት ከመንሳት አልፈው ጥሩ እንቅልፍ እንዳይኖረን ያደርጋሉ።

*መካከለኛ ጥንካሬ ያለው ፍራሽ ለምን ይመከራል?*

የጤና ምርምሮች በግልፅ እንደሚያሳዩት ከሆነ በጣም ጠንካራና ደረቅ ወይም በጣም ለስላሳ ከሆኑት ፍራሾች ጋር ስናወዳድር መካከለኛ ጥንካሬ ያላቸው አፍራሾች ዝቅተኛ የጀርባ ህመም እና ጥራት ያለው እንቅልፍ ያስገኛሉ ።

ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ፍራሾች ፤
-ሌሊቱን ሙሉ ተፈላጊውን የሰውነት መስተካከል ጠብቀን እንድንተኛ ያስችላሉ። ማለትም
-የጀርባ አጥንታችን በስርአት ይደገፋል
-መገጣጠምያዎቻችን ከጫና ይድናሉ
-የሰውነታችን ክብደት በተገቢው ሁኔታ በመላው አካል ላይ ይከፋፈላል ።

ምንም እንኳ የሰውነት ምቾት ከሰው ሰው የሚለያይ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ለማጣቀሻነት የምንጠቀመው የጥንካሬ ደረጃ ከ10 የሚለካ ሆኖ ከ5-7 መካከል ያለው የጥንካሬ መጠን በተመራጭነት ይጠቀሳል ።

*ከግምት ማስገባት ያለብን ጠቃሚ ነገሮች፤*
በሰዎች መካከል እንደ የሰውነት ክብደት ፣ የአተኛኘት ልምድ እና የግል ምቾት ያሉ ልዩነቶች ትክክለኛውን የፍራሽ ውጤት ይወስናሉ።

*የአተኛኘት ሁኔታ፤*
-በጀርባ የሚተኙ ሰዎች ሁሌም መካከለኛ ጥንካሬ ካለው ደጋፊ ፍራሽ ብዙ ያተርፋሉ ።
-በሌላ በኩል በጎን የሚተኙ ሰዎች በመጠኑም ቢሆን ለስለስ ያለ የተሻለ ከጫና የሚያስታግስ ነገር ሊመርጡ ይችላሉ።

*የፍራሹ ይዞታ፤*
በጣም ያረጀና የጎረጎደ ፍራሽ ምንም እንኳ ሲገዛ ጥራት ያለው ቢሆንም የጀርባ ህመምን ሊያባብስ ይችላል።

*መረጃዎቹ ምን ያሳያሉ?*
መካከለኛ ጥንካሬ ያላቸው ፍራሾች አሳሳቢ የታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም ላላቸው ሰዎች እፎይታን ይሰጣሉ እንቅስቃሴንም ያሻሽላሉ።

ብዙ ጊዜ በተለምዶ እንደሚሰማው በጣም ጥብቅና ጠንካራ የሆኑ ፍራሾች የተሻሉ ናቸው የሚለውን ሀሳብ የሚደግፍ መረጃ የለም።
ስንተኛ የሚሰማን ምቾትና ሰውነታችን በስርአት ደገፍ ማለት መቻሉ የእንቅልፍ ጥራትንና የህመም መቀነስን የሚወስኑ ነገሮች ናቸው።

*ዋናው ነገር፤*
በጣም ያልጠነከረና መካከለኛ ፍራሽ አስተማማኝና በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም ለሚሰቃዩ ሰዎች በማስረጃ የተደገፈ ምርጫ ነው። ምክንያቱም ምቾት እየሰጠ የተስተካከለ የጀርባ የአጥንት አቀማመጥ እንዲኖር ስለሚያደርግ ነው።

የሆነ ሆኖ ግን ተመራጩ ፍራሽ ጥሩ እንቅልፍ የሚሰጦትና ሲነጋ ህመም የሌለበት መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

ዶክተር ሲራክ ሀይሉ ከሚኔሶታ
የካይሮፕራክቲክ ሀኪም

*ማስተባበያ*
ይህ ፅሁፍ ለትምህርታዊ አላማ ብቻ የሚውል ነው። በምንም መልኩ በቀጥታ የጤና ባለሙያን ምክር አይተካም። የፍራሽ አጠቃቀም ውጤቱ ከሰውሰው ሊለይ ስለሚችል የጀርባ ህመም ሲሰማዎት እባክዎትን የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

Medium-Firm Mattress and Low Back Pain.

Low back pain is common, and sleep quality plays an important role in how the body recovers. One important factor is your mattress. While no single mattress works for everyone, research suggests that mattress firmness can affect spinal alignment, comfort, and pain levels.
The goal during sleep is to keep the spine in a neutral, supported position. If a mattress is too soft, the body may sink—especially around the hips—leading to poor alignment. If it is too firm, it may create pressure on the hips, shoulders, and natural curves of the spine. Both can contribute to discomfort and poor sleep.
Why Medium-Firm Is Often Recommended
Medium-firm mattresses are commonly recommended because they provide a balance of support and comfort. They may help with:
Spinal support
Pressure relief for joints
Even weight distribution
Better sleep quality
A medium-firm mattress is often described as about 5–7 out of 10 on a firmness scale, although comfort varies from person to person.
Important Considerations
Body weight, sleep position, and personal comfort all matter. Back sleepers may benefit from medium-firm support, while side sleepers may prefer a slightly softer surface for pressure relief. Also, an old or sagging mattress can worsen back discomfort, regardless of its original quality.
Bottom Line
A medium-firm mattress can be a good evidence-based choice for many people with low back pain because it supports spinal alignment while still providing comfort. However, the best mattress is the one that helps you sleep comfortably and wake up with less pain.

Dr. Sirak Hailu
Chiropractic Physician

Educational content only. Individual results may vary. Consult a healthcare professional if pain persists.

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.