ለአርቲስቶች የተለየ የፈጠራ ድባብ ያስፈልጋቸዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ" በሚል በተዘጋጀው መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አርቲስቶች ካላቸው ልዩ ተሰጥኦና የፈጠራ ብቃት አኳያ የሚመጥን ድባብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሳተላይት ከተማ ፕሮጀክት ውስጥ ስለሚገነባው የኪነ-ጥበብ ማዕከል ባደረጉት ገለጻ፣ በግንባታ ላይ ያለው "ግራንድ ሰርክል ሆል" ግማሽ አካሉ ለአርት ጋለሪ እንዲውል ተደርጎ ታስቦ እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህ ተግባር ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለነገውም ትውልድ ጭምር ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።
አርቲስቶች ካላቸው ልዩ የመፍጠር ተሰጥኦ ባሻገር ማንኛውም ሰው ከሚያስብበት መንገድ ወጣ ያለ አመለካከትና የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው በመሆናቸው፣ ለሥራቸውና ለፈጠራቸው ምቹ የሆነና ከልማድ የወጣ አካባቢ እንደሚፈልጉ አብራርተዋል።
ይህን መሰል ለአርቲስቶች ምቹ የሆነ የሥራ ድባብ መፍጠር ለኢትዮጵያ ቀላል ባይሆንም፣ መንግሥት ግን የአርቲስቶችን ልዩ ባህርይና ፍላጎት ከግምት ውስጥ ያስገቡ ማዕከላትን በመገንባት ለዘርፉ ያለውን ክብርና ትኩረት በተግባር እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።
#ebc #ethiopia #pmabiyahmed #artgallery #creativeeconomy #urbandevelopment

1 month ago