Logo
Ethio telecom
ኢትዮ ቴሌኮም እና ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት (BII) የሀገሪቱን የዲጂታል ሽግግር ለማፋጠን በጋራ ለመሥራት ስትራቴጂካዊ ውይይት አደረጉ

የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከዩናይትድ ኪንግደም የልማት ፋይናንስ ተቋም (BII) ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሀገራችን ዲጂታል እና ዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታ ዙሪያ ስትራቴጂካዊ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም ዋና ሥራ አስፈፃሚያችን ኩባንያችን በክላውድ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ በቴሌብር እና በአረንጓዴ ኢነርጂ የታገዘ የተቀናጀ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር በመገንባት የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ እየመራ ስለመሆኑ በዝርዝር አብራርተዋል።

የብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ልዑክ በበኩላቸው ኢትዮ ቴሌኮምን የዲጂታል ኢኮኖሚው ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሞተር መሆኑን በመጥቀስ፤ በዩናይትድ ኪንግደም የሚደገፉ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር እና የ"ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር 2028" ስትራቴጂን በጋራ ለማሳካት ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት ገልጸዋል።

በመጨረሻም ሁለቱ ተቋማት አዳዲስ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለመፍጠር እና በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት በቅንጅት ለመሥራት ተስማምተዋል።

ተጨማሪ፡- http://bit.ly/3QxqNXz

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.