ቤተክርስቲያኗ ለ1600 ወገኖች ማዕድ አጋራች
#ethiopia | የቦሌ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን የ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ 33 ሰንጋዎችን በመግዛት፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች፣ለአረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች፣የቀድሞ ወታደሮች አባላት፣የጎዳና ተዳዳሪዎች፣የቀን ጉርሳቸውን በዕለት ሰርተው የሚያገኙ የቀን ሰራተኞች በማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንደሆኑ የቦሌ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት መጋቢ አመሉ ጌታ ገልጸዋል።
እያንዳንዳችን በበጎ ፈቃዳችን ለድሀዎች በመድረስ እና በማገዝ የድሆች አምባሳደር እንሁን ያሉት ፓስተር አመሉ፣ ቤተክርስቲያኗ በጎፈቃደኛ ግለሰቦችን ፣ ተቋማትንና አብያተ ክርስቲያን በማስተባበር የማዕድ ማጋራት ስታዘጋጅ 14 ዓመታትን አስቆጥራለች ብለዋል።
የቦሌ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን በየወሩ 127 አረጋዊያንን እና 209 ህፃናትን በቋሚነት እየረዳች ነው ያሉት፣መጋቢ አመሉ በየበዓላትም የአልባሳት ስጦታ እንደምትሰጥም ገልጸዋል።
ማዕድ ህብረብሔራዊነታችን ማሳያ ነው ያሉት፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ይህ በጎ ተግባር ዜጎችን በኢኮኖሚና በማህበራዊ ተጠቃሚ ያደረገ ስለመሆኑ አስረድተዋል።
ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ወገኖች በዓሉን በደስታ ማሳለፍ እንዲችሉ እንዲህ አይነት በጎ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ዋና ስራ አሰፈፃማው ተናግረዋል።
የተማሪዎች ምገባን ጨምሮ ሰው ተኮር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የገለፁት ዶ/ር ምስክር፣በእህማማችነት እና በወንድማማችነት መኖር አለብንም ብለዋል።
የካናዳ አብያተ ክርስቲያናትን ወክለው ንግግር ያደረጉት ፓስተር መልኬ፣ይህ በጎ ዓላማ የስጋዊም የመንፈሳዊ ግዴታ ነው።
ያለንን ማካፈልም መፅሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሮም እንደሆነ ገልጸዋል። በማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሩ ላይ፣የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣የሐይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

2 months ago