Logo
FastMereja
የልማት አርበኛዋ ወ/ሮ አልማዝ ሻንቆ ለ40 አባወራዎች የትንሳኤ ማዕድ አጋሩ
#fastmereja I ሚያዝያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም

የልማት አርበኛዋ ወ/ሮ አልማዝ ሻንቆ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን የ116 ሺህ ብር የሰንጋ በሬ እና የዱቄት ድጋፍ አደረጉ።

በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዘይሴ ኤልጎ ሉዳ ቀበሌ ዛሬ በተከናወነው በዚህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ላይ 40 አባወራዎች የቅርጫ ስጋ ተጠቃሚ ሆነዋል። ወ/ሮ አልማዝ ከቅርጫ ስጋው በተጨማሪ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ 10 ኪሎ ግራም የፉርኖ ዱቄት አበርክተዋል።

ተጠቃሚዎቹ በሰጡት አስተያየት ድጋፉ በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ ትልቅ አቅም እንደሆናቸው ገልጸው፣ ለወ/ሮ አልማዝ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.