በትንሳኤ በዓል ላይ የእንስሳት ዋጋ ሊንር የቻለው የእንስሳት መኖ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ እንደሆነ ተነገረ
የፋሲካ በዓል ላይ የእርድ እንስሳት ዋጋ ከየትኛውም ግዜ በላይ ጭማሪ ሊያሳይ የቻለው የእንስሳት መኖ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ እንደሆነ የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ ።የበአል ግብይት ለእርድ የሚቀርቡ እንስሳት በአቅርቦት በኩል ከመቀነሳቸው ሌላ በዋጋም ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ማሳየታቸውን ነዋሪዎቹ ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል።80 እና 90 ሺህ ብር ይሸጡ የነበሩ ዝቅተኛ የእርድ በሬዎች በአሁኑ የገበያ ዋጋ እስከ 153 ሺህ ብር የተሸጡ ሲሆን መካከለኛ የእርድ በሬ ከ163ሺህ ብር እስከ 200 ሺህ ብር እየተሸጡ ይገኛሉ።
እንዲሁም ከፍተኛ ሰንጋ በሬ እስከ 260ሺህ ብር መሸጡንም ነዋሪዎቹ ገልፀው፤ ባለፈው የገና በዓል ወቅት ከነበረው የአንድ እርድ በሬ ዋጋ ላይ የ50 ሺህ ጭማሪ መታየቱን ጠቅሰዋል።የበግ እና የፍየል ዋጋ ከሃያ ሺህ እስከ አርባ አምስት ሺህ ብር የሚጠጋ መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎች ከባለፈው የበዓል ዋጋ ጋር ሲነፃፀር በአንድ የበግ እና ፍየል ዋጋ ላይ እስከ ሰባት ሺህ ብር የዋጋ ጭማሪ መሆኑን ገልጸዋል።
የወተት እና የስጋ አርቢዎች ከዚህ ቀደም በአራት ሺሕ አምስት መቶ ብር የሚሸጠው ምጥን የእንስሣት መኖ እና ከብቶችን የሚያደልበው ጥቁር ፋጉሎ በእጥፍ በመጨመር እስከ ዘጠኝ ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጸዋል። የዶሮ መኖ በተመሳሳይ በኪሎ የሰላሳ ብር ጭማሪ አሳይቷል።የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሂርጻ አዱኛ የእንስሳት መኖ ዋጋ መጨመር ጋር የወተት እና የስጋ እንስሳት አርቢዎች ላይ ተፅዕኖ የፈጠረ ቢሆንም እንስሳትን ቀለብ የሚውሉ አዝርቶችን በራሱ መንገድ በማምረት የዋጋ ንረቱን እንዲቆጣጠር በባለሞያ እገዛ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
የእንስሳት መኖ በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረበት ዋነኛ መንገድ ከወቅታዊ የትራንስፖርት ችግር ጋር ሲሆን ይህ ወቅታዊ ችግር በመሆኑ ወደፊት ባሉ ግዚያት የመኖ ዋጋ ይስተካከላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው በእንስሳት መኖ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
seledadotio

4 months ago