የኤሌክትሪክ መኪና አብዮት፦ ቴስላ እጅግ ርካሽ እና አዲስ የሆነ "SUV" መኪና ሊያመርት ነው!
የዓለማችን ግዙፉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ቴስላ አሁን ካሉት ሞዴሎች በዋጋ እጅግ የሚረክስ እና አነስተኛ መጠን ያለው አዲስ የ"SUV" መኪና ለማምረት ዝግጅት መጀመሩን የሮይተርስ የዜና ምንጮች ገለጹ። ይህ "ሬድውድ" በሚል የኮድ ስም የሚጠራው አዲስ ፕሮጀክት አሁን በገበያ ላይ ካሉት ሞዴል 3 ወይም ሞዴል ዋይ የተቀየረ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አዲስ ዲዛይን የሚኖረው መሆኑ ታውቋል።
የመኪናው ዋጋ ከሌሎቹ የቴስላ ሞዴሎች በከፍተኛ ሁኔታ ቅናሽ የሚደረግበት ሲሆን ይህም ኩባንያው ሰፊውን የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ የያዘው ስትራቴጂ አካል ነው። ተሽከርካሪው ከሞዴል ዋይ በርዝመቱ አጭርና ክብደቱም ቀለል ተደርጎ የሚሰራ ሲሆን ቴስላ ከሳምንታት በፊት ከመለዋወጫ አቅራቢዎች ጋር ሰፊ ውይይት መጀመሩም ተጠቁሟል።
ይህ የምርት ሂደት በዋናነት በቻይናው የሻንጋይ ፋብሪካ እንደሚጀምርና ወደ አሜሪካና አውሮፓ እንደሚስፋፋ ይጠበቃል። የቴስላ ይህ እርምጃ በአሁኑ ወቅት በአነስተኛ ዋጋ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በብዛት እያመረቱ ካሉ የቻይና ኩባንያዎች ጋር ያለውን ፉክክር ለማጠናከር የሚረዳው ሲሆን መኪናው ለገበያ ሲበቃ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ተደራሽነት በእጅጉ ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል።
seledadotio

2 months ago