Logo
Getu Temesgen
የጸሎተ ሐሙስ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተከበረ

​#ethiopia |​ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሕጽበተ እግርና የጸሎተ ሐሙስ በዓልን በፒያሳ በሚገኘው የልደታ ማርያም ካቴድራል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች አክብራ ውላለች።

በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ተገኝተው የሕጽበተ እግር ሥርዓቱን መርተዋል።

ብፁዕነታቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እግር በማጠብ ያሳየውን የትሕትና እና የአገልግሎት ምሳሌነት በማሰብ የምእመናንን እግር አጥበዋል።

​በዕለቱ በተከናወነው የቅዳሴ ጸሎትና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ላይ በርካታ ምእመናን የተገኙ ሲሆን፣ የክርስቶስን ሕማማትና የመጨረሻውን የእራት ግብዣ የሚያዘክሩ ጸሎቶችም በጋራ ቀርበዋል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለምእመናኑ ባስተላለፉት መልእክት የጸሎተ ሐሙስን መንፈሳዊ ትርጉምና የእርስ በእርስ መዋደድን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።

ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
📷 EBC

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.