ዶ/ር ቴድሮስ በጎጃም በጤና ባለሙያዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ፤ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግም ጠየቁ
#fastmereja I የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በአማራ ክልል ሰሜን ሜጫ ወረዳ በሦስት የጤና ባለሙያዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በጽኑ ማውገዛቸውን ገለጹ። ዋና ዳይሬክተሩ ድርጊቱን አስመልክቶ ባወጡት መግለጫ፣ በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ እንዳመለከቱት፣ የጤና ባለሙያዎች በማንኛውም የግጭት ወቅት ጥበቃ ሊደረግላቸው የሚገባና ለሰዎች ሕይወት መታደግ የሚሠሩ ወገኖች ናቸው። "የጤና ባለሙያዎች በማንኛውም ጊዜ ጥበቃ ሊደረግላቸውና ለሚያስፈልጋቸው ሰው ሁሉ ሕይወት አድን ሥራዎቻቸውን ሊያከናውኑ ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።
ሰለባዎቹ በአብዮት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያና በግል ተቋም ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ባለሙያዎች መሆናቸው ይታወቃል። ዋና ዳይሬክተሩ የዓለም ጤና ድርጅት በጉዳዩ ላይ ያለውን ጥብቅ አቋምና የገለልተኛ ምርመራ አስፈላጊነት በአጽንኦት ገልጸዋል።

2 months ago