ዳጎስ ያለ ሽልማት የሚያሸልመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቴምር ፕሮፐርቲስ የሼባ ማይልስ ሽልማት የሚያበረክቱበትን ስምምነት በይፋ ፈርመዋል
#ethiopia | "በቤትዎ አለምን ይዙሩ" በሚል መሪ ቃል ሁለቱ ተቋማት ስምምነት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቴምር ሪልስቴት ደንበኞች ቤት በሚገዙበት ወቅት የአየር መንገዱን የነጻ ጉዞ እና የሌሎች አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን የሼባ ማይልስ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።
ስምምነት የአየር መንገዱን የቋሚ ደንበኞች መርሃ ግብር (ShebaMiles) ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ለሪልስቴቱ ደንበኞች ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር የታለመ መሆኑን ገልጸዋል።
"እኛ የምንገነባው ቤትን ብቻ ሳይሆን እምነትንም ነው" የቴምር ፕሮፐርቲስ ጀነራል ማናጀር አቶ ጃፋር መሀመድ።
አቶ ጃፋር መሀመድ የቴምር ሪልስቴት ደንበኞች ለሚገዙት ቤት በከፈሉት የገንዘብ መጠን ልክ የሼባ ማይልስ ነጥቦችን የሚያገኙ ይሆናል ብለዋል።
የቤቱን ዋጋ እስከ 50 በመቶ ለሚከፍሉ ደንበኞች ለእያንዳንዱ አንድ ዶላር (ወይም በወቅታዊ ምንዛሬ ተመጣጣኝ ብር) 2.5 ማይልስ ይሰጣል ተብሏል።
ከጠቅላላ የቤት ዋጋው 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ ለእያንዳንዱ አንድ ዶላር 3.5 ማይልስ ሽልማት እንደሚበረከት ተገልጿል።
ደንበኞች በሚያገኙት ነጥብ መሰረት የአባልነት ደረጃቸውን ከብሉ ወደ ሲልቨር፣ ከሲልቨር ወደ ጎልድ እንዲሁም ወደ ከፍተኛው የፕላቲነም ደረጃ የሚያድርገ መሆኑም ተጠቁሟል።
የቴምር ሪልስቴት የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ድርጅቱ የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት እያከበረ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ ከአየር መንገዱ ጋር የተደረገው ስምምነት ለደንበኞቻቸው ካላቸው ክብር የመነጨ መሆኑን ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

4 months ago