"ራያ የአለማችን ምርጡ ነው!" — ሚኬል አርቴታ
#ethiopia | የመድፈኞቹ አለቃ ሚኬል አርቴታ በግብ ጠባቂያቸው ዴቪድ ራያ ብቃት መደሰታቸውን በቀጥታ ገልጸዋል።
አርቴታ ራያን "የአለማችን ምርጡ ግብ ጠባቂ" ሲሉ የጠሩት ሲሆን፣ ክለቡ እንዲህ አይነት ተጫዋች በማግኘቱ ትልቅ እድለኛ እንደሆነም በኩራት ተናግረዋል።
> "ወደ እኛ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ነው፤ እሱ ከእኛ ጋር በመኖሩ በእውነት እድለኞች ነን" — አርቴታ
አርሰናል አሁን ካለበት ደረጃ አንጻር አሰልጣኙ ጥንቃቄ የተሞላበት ግን ተስፋ ሰጪ አስተያየት ሰጥተዋል። "ግማሽ መንገዱን ተጉዘናል" ያሉት አርቴታ፣ አሁን የሚቀረው በኤምሬትስ ስታዲየም በደጋፊዎች ፊት ስራውን በአግባቡ ማጠናቀቅ እንደሆነ አሳስበዋል። ይህ ከተሳካ ደግሞ "ትልቁን ህልም" ማለም እንደሚጀምሩ ፍንጭ ሰጥተዋል።
አርቴታ ስለ ጀርመናዊው ኮከብ ካይ ሀቨርትዝ ሲናገሩም አድናቆታቸውን አልደበቁም። ሀቨርትዝ ትላልቅ አጋጣሚዎችን እና ወሳኝ ጨዋታዎችን እንደሚወድ የገለጹት አሰልጣኙ፣ "በአስፈላጊ ሰዓት መገኘት ከአንድ ትልቅ ተጫዋች የምንፈልገው ዋናው ነገር ነው" ሲሉ የተጫዋቹን አስፈላጊነት አስምረውበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #arsenal #mikelarteta #davidraya #kaihavertz #gunners #footballnews #ethiopia #የመድፈኞቹ_ቤት

4 months ago