Logo
YenetaTube
ምክር ቤቱ የተሻሻለውን የባለብዙ ተዋንያን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትና አስተዳደር አዋጅን አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻሻለውን የባለብዙ ተዋንያን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትና አስተዳደር አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ የምክር ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን እና የተሻሻለውን የባለብዙ ተዋንያን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በሚመለከት ከግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና ውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ ሪፖርቱንና የውሳኔ ሃሳቡን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለግብርና ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች።

የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትን ተደራሽነት ለማስፋት፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አዋጅ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

አዋጁ በዚህ ረገድ የግብርና ቴክኖሎጂን ማስተዋወቅና ጥቅም ላይ ማዋል እንዲሁም የግብርና ቢዝነስን ለማስፋት ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅን እና የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።

#ኢዜአ

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.