ኢራን በኩዌትና በባህሬን የነዳጅ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ፈጸመች!
በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት አድማሱን በማስፋት፣ ኢራን በዛሬው ዕለት በኩዌትና በባህሬን የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ብርቱ ጥቃት መፈጸሟ ተሰማ።የኩዌት ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው፣ ኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በሀገሪቱ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሰንዝራለች።በጥቃቱ ሳቢያ በተቋማቱ ላይ ከፍተኛ ቃጠሎና መጠነ ሰፊ የቁሳዊ ንብረት ውድመት መድረሱን የመንግሥቱ የነዳጅ ኮርፖሬሽን ገልጿል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ኢራን በባህሬን በሚገኙ ሁለት የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት የፈጸመች ሲሆን፣ በሁለቱም የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ ከፍተኛ ቃጠሎ ተከስቶ እንደነበር ተዘግቧል።የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የቻሉ ሲሆን፣ የባህሬን ባለሥልጣናት በጥቃቱ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጠዋል። አዣንስ ፍራንስ ፕረስና የጀርመን ዜና አገልግሎት እንደዘገቡት፣ ይህ የኢራን እርምጃ በክልሉ ያለውን የነዳጅ ገበያና የጸጥታ ሁኔታ ይበልጥ ስጋት ላይ ጥሎታል።
Via DW
seledadotio

2 months ago