ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ በቦሌ አትላስ ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች ለሽያጭ አቀረበ!
#fastmereja : በኮንስትራክሽን ዘርፍ የአሥር ዓመታት ልምድ ያለው ኮምፓስ ኮንስትራክሽን (ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ)፣ በቦሌ አትላስ አካባቢ ያስገነባቸውን ባለ 15 ወለል ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንቶች ለሽያጭ ማቅረቡን በዛሬው ዕለት ባከናወነው የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አስታወቀ።
ለገበያ የቀረቡት እነዚህ አፓርትመንቶች ከባለ አንድ እስከ ባለ ሦስት መኝታ ክፍሎችን የያዙ ሲሆን፣ የቤቶቹ የቆዳ ስፋትም እንደ ፍላጎቱ ከ80 ካሬ ሜትር እስከ 160 ካሬ ሜትር የሚሸፍኑ መሆናቸው በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገልጿል።
የኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ማርኬቲንግ ማናጀር ወ/ሪት ማርታ ወርቁ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ ቤቶቹን ለገበያ ያቀረበው ምቹ የክፍያ አማራጮችን በማካተት ሲሆን ይህም የቤት ገዢዎች ከ800 ሺህ ብር ጀምሮ በሚከፈል ቅድመ ክፍያ ወይም በ8 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ መነሻ ዋጋ የቤቶቹ ባለቤት መሆን የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን ገልፀዋል።
እንዲሁም ተቋሙ በአሁኑ ወቅት በቦሌ አትላስ ከሚገኘው ግንባታ በተጨማሪ፣ በካዛንችስ አካባቢ የንግድና የመኖሪያ ቤቶችን በአንድ ላይ የያዘ ባለ 19 ወለል ህንፃ ግንባታ በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ተመላክቷል።
ኮምፓስ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለፉት አሥር ዓመታት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ በነበረው ቆይታ፤ በተለይም ከታላላቅ ሪል ስቴቶች ጀርባ በመሆን የህንፃ መዋቅር (Structure) ስራዎችን በጥራት ገንብቶ በማስረከብ ይታወቃል።
ድርጅቱ በቅርብ ጊዜያት ወደ ሪል ስቴት ዘርፉ ከተቀላቀለ በኋላ በመስቀል ፍላወር እና በቄራ አካባቢዎች ያስገነባቸውን ዘመናዊ አፓርትመንቶች በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ለደንበኞች ማስረከቡ ተነግሯል።

2 months ago