አብራሪዎቹን በህይወት ለያዘ ወይም ለፖሊስ አሳልፎ ለሰጠ ሰው ትልቅ ሽልማት አዘጋጅቻለሁ - ኢራን
የኔታ ሚዲያ
የአሜሪካ የጦር ጄት በኢራን ሰማይ ላይ ተመትቶ ወደቀ የአብራሪውን የነፍስ አድን ፍለጋ ተጀምሯል
ዛሬ ዐርብ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አንድ የአሜሪካ የጦር ጄት በኢራን የአየር ክልል ውስጥ ተመትቶ መውደቁን የአሜሪካ እና የኢራን ምንጮች አረጋገጡ።
ይህ ክስተት በአሁኑ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት አሜሪካ የጦር አውሮፕላን ሲመታባት የመጀመሪያው ነው።
መጀመሪያ ላይ የወጡ ዘገባዎች አውሮፕላኑ F-35 እንደሆነ ቢገልጹም በኋላ ላይ የወጡ የፎቶ እና የቪዲዮ መረጃዎች ግን የተመታው አውሮፕላን F-15E Strike Eagle ሳይሆን እንዳልቀረ አመልክተዋል።
አውሮፕላኑ በደቡብ ምዕራብ ኢራን ኹዜስታን በተባለ ግዛት ውስጥ መውደቁ ተነግሯል።
አሜሪካ የአውሮፕላኑን አብራሪዎች ለመፈለግ መጠነ ሰፊ የነፍስ አድን ዘመቻ መጀመሯ ተገልጿል የሲ.ኤን.ኤን መረጃ እንደሚያመለክተው የአሜሪካ ሄሊኮፕተሮች በኢራን ሰማይ ላይ ዝቅ ብለው ሲበሩ የታዩ ሲሆን ይህም አብራሪዎቹን ለማግኘት የሚደረግ ጥረት አካል መሆኑን ተጠቅሷል
የኢራን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን አብራሪዎቹን በህይወት ለያዘ ወይም ለፖሊስ አሳልፎ ለሰጠ ሰው ትልቅ ሽልማት እንደሚሰጥ በማስታወቅ ላይ ናቸው።
አብራሪዎቹ ከአውሮፕላኑ ውስጥ በፓራሹት ወጥተው ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ የመቀመጫ ስብርባሪዎች በምስል ታይተዋል።
እስከ አሁን ድረስ የኋይት ሀውስም ሆነ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ስለ አብራሪዎቹ ደህንነትና ሁኔታ ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም።
ይህ ክስተት የተከሰተው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃቱ እንደሚቀጥል በዛቱ ማግስት ነው።
ትራምፕ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ "ኢራንን ወደ ድንጋይ ዘመን እንመልሳታለን" ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በተለይም በኢራን ድልድዮች እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዘር አስጠንቅቀው ነበር።
የአውሮፕላኑ መመታት ቀጠናው ወደ ከፋ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። በተለይም በሆርሙዝ ስትሬት በኩል የሚደረገው የነዳጅ ዝውውር መስተጓጎሉ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

2 months ago