ኩባ ከ2,000 በላይ እስረኞችን ልትፈታ ነው
የኔታ ሚዲያ
የኩባ መንግሥት "ሰብዓዊና ሉዓላዊ እርምጃ" በሚል ከ2,010 በላይ እስረኞችን ለመፍታት መወሰኑን ሐሙስ ዕለት አስታውቋል።
ይህ ውሳኔ የተሰማው ሀገሪቱ ከአሜሪካ የሚሰነዘርባትን ከፍተኛ የፖለቲካ ጫና እየተጋፈጠች ባለችበት ወቅት ነው።
በአሜሪካ የሚገኘው የኩባ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ መሠረት የውጭ ሀገር ዜጎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አረጋውያን ይገኙበታል።
በኩባ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት የተለመደ ተግባር እንደሆነና ከትንሣኤ (Holy Week) ሃይማኖታዊ በዓላት ጋር ተያይዞ የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።
የምሕረት ብቁነት የተለየው በፈጸሙት ወንጀል ዓይነት፣ በእስር ቤት በነበራቸው መልካም ሥነ-ምግባር፣ ከቅጣታቸው ውስጥ ከፍተኛውን ጊዜ በማጠናቀቃቸው እና በጤና ሁኔታቸው ላይ ተመርኩዞ መሆኑ ተጠቁሟል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጭ ቤተ መንግሥት ከተመለሱ በኋላ በኩባ የኮሚኒስት አመራር ላይ ለውጥ እንዲመጣ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው። በተለይም ወደ ደሴቷ የሚላኩ የነዳጅ ጭነቶችን በማገዳቸው፣ በሀገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረትና የኃይል መቆራረጥ ተከስቷል።
ባለፈው ሳምንት ግን ከጥር ወር ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ 730,000 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የጫነች የሩሲያ መርከብ ኩባ ወደብ መድረሷ ይታወሳል።
እንደ ሂውማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) መረጃ ከሆነ ኩባ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን በእስር ላይ የምታቆይ ሲሆን በመንግሥት ተቺዎች ላይም ወከባና የወንጀል ክስ መመስረት ይስተዋላል።
ይህ በዘንድሮው የፈረንጆች ዓመት ኩባ እስረኞችን ስትፈታ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባለፈው መጋቢት ወር ከቫቲካን ጋር በተደረገ ንግግር 51 እስረኞች መፈታታቸው ይታወሳል። እንዲሁም በ2025 በቫቲካንና በአሜሪካ አደራዳሪነት 553 እስረኞች ተፈትተው ነበር።

4 months ago