Logo
YenetaTube
በአዲስ አበባ ከተማ የተባበሩት አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ በአንድ ሰው ላይ የሞትና በሦስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡00 ሠዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው የተባበሩት አደባባይ አካባቢ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3A-41968 አ/አ የሆነ አልያንስ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከአቤም ወደ የተባበሩት አቅጣጫ ቁልቁለቱን በመጓዝ ላይ ሳለ ከአያት ወደ ሲ.ኤም.ሲ አቅጣጫ እየተጓዙ ከነበሩ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-35090 አ/አ እና የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3B-57071 አ/አ ቪትዝ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በመግጨት የተባበሩት አደባባዩ ላይ በመውጣት ሊገለበጥ ችሏል፡፡

በአደጋውም የፒካፕ መኪናው አሽከርካሪ ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በውስጡ ተሳፍረው የነበሩ ሁለት የ7ኛ እና የ5ኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች እንዲሁም የቪትስ መኪናው አሽከርካሪ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

አሽከርካሪዎች ሁሌም ቢሆን የመንገዱን ሁኔታና አቀማመጥ በሚገባ በማጤን ተሽከርካሪያቸውን መቆጣጠር በሚያስችላቸው ሁኔታ ሊያሽከረክሩ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን እያስተላለፈ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ለተጎጂዎችም ብርታትን ይመኛል፡፡

Addis Ababa police

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.