Logo
Getu Temesgen
ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከዘፈኑ ዓለም ራሱን አሰናበተ
#ethiopia | ታዋቂው ወጣት ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከዓለማዊ ሙዚቃ (ዘፈን) ሙሉ በሙሉ መውጣቱንና ወደ ቀድሞ መንፈሳዊ ህይወቱ መመለሱን በይፉ አስታወቀ።

አርቲስቱ ይህንን ውሳኔውን ያስታወቀው በይፋዊው የፌስቡክ ገጹ ሲሆን፣ የዘፈኑን ዓለም "ውስብስብና አጋንንታዊ አሰራር ያለበት" ሲል ገልጾታል።

አቤል ላለፉት ዓመታት በሙዚቃው ዓለም በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ ከፍተኛ ውስጣዊ ትግል ሲያደርግ እንደነበር ገልጿል። በተለይም ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ዓመታት ሙዚቃን አቁሞ እንደነበር አስታውሶ፣ በወቅቱ ወደ ዘፈኑ ዓለም ዳግም መመለሱ ጸጸት እንደፈጠረበት አልሸሸገም።

"ዓለም ውሸት ነው፤ ዝናም ከንቱ ቆሻሻ ነው! የውሸት መልክና የውሸት ፈገግታ ብቻ!" ሲል አቤል አሁን ያለውን አቋም በጽኑ ቃላት ገልጿል።

ድምፃዊው ለውሳኔው መነሻ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች (2ኛ ጴጥሮስ 2፥22 እና ዕብራውያን 10፥38) በመጥቀስ፣ ወደ ኋላ ማፈግፈግ አብቅቶለታል ብሏል።
ለዚህም ለውጡ የጸለዩለትን ሁሉ አመስግኗል።

አቤል ሙሉጌታ ከዚህ በኋላ ወደ ዘፈኑ ዓለም ዳግም እንደማይመለስና ህይወቱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠቱን በማረጋገጥ መልዕክቱን አጠቃሏል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.