የሀገሬን ምድር ለሚረግጡ የአሜሪካ እግረኛ ወታደሮች እሳት አዘንብባቸዋለው - ኢራን
አንደኛ ወሩን ያስቆጠረው እስራኤልና አሜሪካ ከኢራን ጋር እያደረጉት የሚገኘው ጦርነት አሁንም በርካታ ጉዳቶችን እያስከተለ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የቀጣናው ጦርነት እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት አሜሪካ ከ3 ሺህ 500 በላይ እግረኛ ወታደሮችንና የጦር መርከቧን በመካከለኛው ምሥራቅ አሰማርታለች፡፡
የዋሺንግተን እግረኛ ወታደሮች በኢራን ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ ዝግጁ መሆናቸውንም የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡
ይህን ተከትሎም፤ ኢራን “በቀጣናው ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ በሚል ወደ መካከለኛው ምስራቅ የደረሱ የአሜሪካ ወታደሮችን በተጠንቀቅ እየጠበኩ ነው” ብላለች፡፡
የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ ሞሃማድ ባግሄር ጋሊባፍ ÷ አሜሪካ ለንግግር ፍላጎት እንዳላት እየገለጸች በቴህራን የእግረኛ ወታደራዊ ዘመቻ ለመካሄድ መዘጋጀቷን ኮንነዋል፡፡
የኢራን ጦር የትኛውንም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ ነው ያሉት አፈ ጉባዔው ÷ ጦሩ ወደ ኢራን በሚገቡ የአሜሪካ እግረኛ ወታደሮች ላይ እሳት ለማዝነብ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢራን በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እና በባህሬን የአልሙኒየም መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ቴህራን በኩዌት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት የራዳር መቆጣጠሪያ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷ ተጠቁሟል፡፡
seledadotio

2 months ago