Logo
SeledaPost
የኢራን እስላማዊ አብዮት ዘብ ማሳሰቢያ

የኢራን እስላማዊ አብዮት ዘብ ስቪል ዜጎች በቀጠናው ካሉ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች እራሳቸውን እንዲያርቁ አሳሰበ። አብዮታዊ ዘቡ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ «ፈሪዎቹ የአሜሪካና የፅዮናዊት እስራኤል ሃይሎች ስቪሎች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች እና ንጹሃን ስቪሎች እንደ ሰብአዊ ጋሻ እየተጠቀሙ ነው» ብሏል።

በመሆኑም «እራሳችሁን ከጥቃት ለመከላከል አሜሪካውያን ወታደሮች ከሰፈሩባቸው ቦታዎች እራሳችሁን አርቁ» ሲል ማሳሰቡን የዘገበው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ነው።

seledadotio
seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.