የባህረ ሰላጤው ምክር ቤት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ለሚያልፉ መርከቦች ክፍያ እያስከፈለች ነው ሲል ወቀሰ
የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ፤ ኢራን መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል በሰላም እንዲያልፉ ‹‹ክፍያ እየጠየቀች ነው››ሲሉ ከስሰዋል።
ጃሲም መሐመድ አል-ቡዳይዊ ባህሬንን፣ ኩዌትን፣ ኦማንን፣ ኳታርን፣ ሳዑዲ ዓረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ያቀፈውን የስድስቱን የባህረ ሰላጤው ሀገራት ጥምረትን ይመራሉ።
ከዓለም የነዳጅ እና የተፈጥሮ ፈሳሽ ጋዝ አቅርቦት ውስጥ ከ20 እስከ 25 በመቶ የሚሆነው አብዛኛውን ጊዜ በዚህ የውሃ መስመር በኩል ያልፋል።
ሆኖም አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከጀመሩ ከዛሬ አራት ሳምንታት ገደማ ጀምሮ ቴህራን መስመሩን ዘግታዋለች።
አል-ቡዳይዊ ሲናገሩ፤ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋት የንግድ መርከቦች እና የነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንዳያልፉ በመከልከል እና ወሽመጡን ለመሻገር ክፍያዎችን በመጠየቅ በዓረብ ባህረ ሰላጤ አካባቢ የምታሳየው መረጋጋትን የሚያናጋ ባህሪ ሁሉንም ገደቦች አልፏል ብለዋል።
አል-ቡዳይዊ እገዳውን፤ የተባበሩት መንግሥታት የባሕር ሕግ ስምምነትን በግልጽ የጣሰ ነዉ ሲሉ ገልጸውታል።
ይህ ስምምነት ለዓለም አቀፍ መርከቦች ‹‹ያለ ምንም እንቅፋት››የመተላለፍ መብትን ያረጋግጣል።
ምንም እንኳን ቴህራን ይህንን ስምምነት ባታጸድቅም፤ደንቦቹ በልማዳዊ ዓለም አቀፍ ሕግ ሥር የሚወድቁ በመሆናቸው ለሁሉም አገራት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
በአንድ በኩል ኢራን በሌላ በኩል ደግሞ ኦማን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሚገኙበት በዚህ ወሳኝ የባህር መስመር ላይ ኢራን የጉምሩክ ወይም የማለፊያ ክፍያ እያስከፈለች ነው በማለት የከሰሱ የመጀመሪያው ከፍተኛ የቀጣናው ባለሥልጣን ናቸው።
ለአንዳንድ መርከቦች መደበኛ ባልሆነ መንገድ እና እንደ ሁኔታው ታይቶ ለአንድ ጉዞ እስከ 2 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ ክፍያ እየተጠየቀ መሆኑ እየተዘገበ ይገኛል።
ሰፊው ቀጣናዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በዚህ የውሃ መስመር በኩል ያለፉት ጥቂት መርከቦች ብቻ ናቸው።
እስከዳር ግርማ

2 months ago