"የአሜሪካ ወታደሮችን የሚያስተናግዱ ሆቴሎች ጥቃት ሊሰነዘርባቸው ይችላል" ስትል ኢራን አስጠነቀቀች
👉ማስጠንቀቂያው በጅቡቲ ያሉ ሆቴሎችንም ይመለከታል
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ሆቴሎች የአሜሪካ ወታደሮችን ማስተናገድ እንዲያቆሙ ከበድ ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጡ።
ሚኒስትሩ አሜሪካ ወታደሮቿን ከወታደራዊ ካምፖች አውጥታ በሲቪል ሆቴሎች እና ቢሮዎች ውስጥ በማስፈር የባህረ ሰላጤው አገራት ዜጎችን እንደ "የሰው ጋሻ" እየተጠቀመች ነው ሲሉ ከሰዋል።
እንደ ፋርስ የዜና ወኪል ዘገባ፣ ማስጠንቀቂያው በባህሬን፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በሶሪያ እና በጅቡቲ የሚገኙ ሆቴሎችን ያጠቃልላል።
ኢራን እነዚህን መገኛዎች በዝርዝር መለየቷን የገለጸች ሲሆን፣ ወታደሮቹን ማስተናገድ የማይቆም ከሆነ ተቋማቱ "ህጋዊ የመከላከያ ኢላማ" ተደርገው ጥቃት እንደሚሰነዘርባቸው አስታውቃለች።
ይህ "ሁሉን አቀፍ እና የመጨረሻ" የተባለው ማስጠንቀቂያ፣ ቀጣናዊ ውጥረቱን ይበልጥ አባብሶታል።

2 months ago