በኮሎምቢያ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ የ66 ሰዎች ህይወት አለፈ
በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኮሎምቢያ አንድ 125 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ወታደራዊ አውሮፕላን በመከስከሱ ቢያንስ የ66 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተረጋገጠ። አደጋው የደረሰው አውሮፕላኑ ከሀገሪቱ ደቡባዊ ግዛት ፑቱማዮ ከሚገኘው ፖርቶ ሌጊዛሞ አየር ማረፊያ ተነስቶ ብዙም ሳይቆይ ነው።
የኮሎምቢያ መከላከያ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እንደገለጹት፣ 'ሎክሂድ ማርቲን' (Lockheed Martin) የተባለ ኩባንያ ያመረተው ሲ-130 ሄርኩለስ (C-130 Hercules) አውሮፕላን ከአየር ማረፊያው ከተነሳ 1.5 ኪሎ ሜትር ብቻ እንደተጓዘ መሬት በመምታቱ በእሳት ተያያዘ። አውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ጥይቶችና ፈንጂዎች በመፈንዳታቸው አደጋውን የከፋ እንዳደረገው ተገልጿል።
የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች አዛዥ ጀነራል ሁጎ አሌሃንድሮ ሎፔዝ ባሬቶ እንዳስታወቁት፣ በአደጋው 66 ወታደሮች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ አራት ወታደሮች ደግሞ እስካሁን አልተገኙም። በደርዘን የሚቆጠሩ ሌሎች ወታደሮችም ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአካባቢው ምክትል ከንቲባ ካርሎስ ክላሮስ ለሚዲያ እንደገለጹት፣ በከተማዋ ያሉ ሁለት ክሊኒኮች የቆሰሉትን ወታደሮች ለማከም ጥረት እያደረጉ ሲሆን፣ ጉዳቱ የጸናባቸው ደግሞ በልዩ አውሮፕላኖች ወደ ዋና ከተማዋ ቦጎታ ለተሻለ ህክምና ተልከዋል።
መከላከያ ሚኒስትሩ እና የጦር አዛዡ አደጋው ከህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት ጋር የተያያዘ መሆኑን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ምልክት እስካሁን አለመገኘቱን አረጋግጠዋል። የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ በምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም ታውቋል።
ፑቱማዮ ግዛት ከኢኳዶር እና ከፔሩ ጋር በምትዋሰንበት የአማዞን ደን ውስጥ የምትገኝ ሲሆን አደጋው የደረሰበት አውሮፕላን በጫካው ውስጥ ተሰባብሮ እንደሚገኝ ተዘግቧል።
የኔታ ሚዲያ — ፈጣን እና ተዓማኒ መረጃ!

3 months ago